• Striving for eco industrial park
logo

በነፃ ንግድ ቀጣና ለሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች የተሻለ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጥሪ አቀረበ

በነፃ ንግድ ቀጣና ለሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች የተሻለ የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጥሪ አቀረበ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ለሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች የተሻለ፣ ተደራሽና ውጤታማ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲሰጥ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ጥሪ አቀረቡ።

ጥሪው የቀረበው “ለተወዳዳሪ ነፃ ንግድ ቀጣናዎች የፋይናንስ አገልግሎት ልህቀት” በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ በተካሄደውና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጋራ ባዘጋጁት ወርክሾፕ ላይ ነው።

የኢፓልኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍጹም ከተማ በንግግራቸው፣ በፋይናንስ ዘርፉና በኢንቨስትመንት ልማት ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የተቋማት በጋራ መሥራት ለሀገራዊ እድገት የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና መጫወት መቻል የጋራ ተጠቃሚነትን እድሚያሳድግ የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው በነጻ ንግድ ቀጠናዎች ያሉ የፋይናንስ አገልግሎት ክፍተቶች ሊፈቱና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መፍትሔ ሊፈጥሩ ይገባል ብለዋል።

ኢፓልኮ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የወጪ ንግድ አፈጻጸም ውስጥ 42 በመቶ ድርሻ እንዳለው የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የባለሀብቶችን የፋይናንስ ፍላጎት መደገፍ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል። በተጨማሪም የተቋማትን ቅንጅት በማሻሻል እና የነፃ ንግድ ቀጣናዎችን አቅም በማሳደግ ኢትዮጵያን በሌላ ሀገር ላይ ያላትን ጥገኝነት መቀነስ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ወደ 60 የሚጠጉ ባለሀብቶች በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቁመዋል።

በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብዱላሂ አደም ዩሱፍ ድሬ ዳዋ የኢትጵያውያን የጋራ ቤት መሆኗን ጠቅሰው የሀገሪቱን የልማት ግቦች ለማሳካት የሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ድሬዳዋ በከተማ አስተዳደሩና በኢፓልኮ የሚተዳደሩ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዳሏት ጠቅሰው፣ ከተማዋ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ኢንዱስትሪዎችን በክላስተር ለማደራጀት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር መልዕክት ሳህሉ በበኩላቸው፣ ወርክሾፑን በይፋ ሲከፍቱ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎችን ለመፍጠር ከመሠረተ ልማት በተጨማሪ ቀልጣፋና ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎትን ማሟላት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የባለሀብቶችን የፋይናንስ ፍላጎት የሚመልሱ ተግባራዊና ውጤታማ መፍትሔዎች ላይ መድረስ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ወርክሾፑ በፋይናንስ ተቋማትና በኢንቨስትመንት ልማት ተቋማት መካከል ቅንጅትን ለማጠናከር፣ ያሉ የአገልግሎት ክፍተቶችን ለመለየትና በነፃ ንግድ ቀጣናዎች ለሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች የተሻለ የፋይናንስ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉ ተግባራዊ መፍትሔዎችን ለመለየት ያለመ ነው።
 
IPDC Calls for Stronger Financial Support for Investors in Dire Dawa Free Trade Zone

The CEO of Industrial Parks Development Corporation has called on Ethiopia’s financial sector institutions to strengthen financial services for investors operating in Free Trade Zone (FTZ) to enhance its competitiveness and investment potential.

The call was made during a workshop held in Dire Dawa under the theme “Financial Service Excellence for Competitive Free Trade Zones,” organized by IPDC and the National Bank of Ethiopia (NBE).

Delivering the keynote address, IPDC CEO Fitsum, Ketema emphasized the need for stronger collaboration between the financial sector and investment institutions to address financial service gaps and create mutually beneficial solutions.

He noted that IPDC contributes 42 percent of Ethiopia’s national export performance and highlighted the importance of supporting investors to further strengthen the country's export capacity.

He also underscored the need to improve institutional coordination and reduce Ethiopia’s dependence on other country by maximizing the potential of its free trade zones.

Currently, close to 60 investors are operating in the IPDC administered Dire Dawa Free Trade Zone.

In his opening remarks, Dire Dawa City Administration Mayor Abdulahi Aden Yusuf highlighted that Dire Dawa is the melting pot of Ethiopia. The mayor underscored the importance of domestic financial institutions in financing the country's development ambitions.

He noted that Dire Dawa hosts two industrial parks, administered by the City Administration and IPDC, respectively, and reaffirmed the city's commitment to attracting investment and promoting industrial clustering.

Ethiopian Investment Commission Deputy Commissioner, Melkite Sahilu, opening remark meanwhile, emphasized that competitive investment destinations require not only hard infrastructure but also strong soft infrastructure, particularly efficient financial services. She called for practical and workable solutions to address investors' financial needs.

The workshop brought together relevant stakeholders to strengthen coordination between financial institutions and investment development organizations and identify concrete measures to improve financial services for investors in Ethiopia's free trade zones.