በባህር ዳር ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ500 ሚሊዮን ብር ካፒታል ከበቆሎ ምርት ስታርች ለማምረት ስራ የጀመረው ሃገር በቀል ኩባንያ የማሽን ተከላ ስራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡
በ2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ኢንቨስትመንት በዘመናዊ መንገድ እንጆሪ እና ለመድሃኒት ግብዓት የሚውል ሳፍሮን የተሰኘ አበባ በማምረት ለውጪ ገበያ የሚያቀርብ አፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ የተሰኘ ኩባንያ ወደ ስራ ሊገባ ነው፡፡
በቶክዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተካሄደው የ33ኛዉ ኤዢያ፤ አረብ እና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች ለቅድመ-ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችና ነጻ የንግድ ቀጠና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ካሳዩ የጃፓን ባለሀብቶች ጋር በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውይይት ተካሂዷል ፡፡