ዋና ሥራ አስፈጻሚው ከቻይና የንግድ ድርጅቶች አስተዳደር ማኅበር አመራሮች ጋር ተወያዩ
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ከተማ፣ በቻይና የንግድ ድርጅቶች አስተዳደር ማኅበር (Association of China Commercial Enterprise Management – ACCEM) ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ዣኦ ዚቸን (Ms. Zhao Zichen) ከተመራው ልዑክ ጋር በሁለቱ ተቋማት መካከል ሊኖሩ በሚችሉ የትብብር ዕድሎችና የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሊያደርጉ በሚችሉት ተሳትፎ ዙሪያ ተወያዩ።
በውይይቱ ወቅት አቶ ፍጹም ከተማ፣ ኮርፖሬሽኑ የተቀናጀ የኢንዱስትሪ መሠረተ ልማትን ለባለሀብቶች በማቅረብ፣ ባለሀብቶች በአጭር ጊዜ ወደ ምርት ሥራ እንዲገቡ ለማስቻልና የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማፋጠን እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል።
ኮርፖሬሽኑ በሥሩ 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችንና ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሚያስተዳድር የመንግሥት ልማት ድርጅት መሆኑን ያስረዱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የACCEM አባላት ሀብታቸውን እና ዕውቀታቸውን በኢትዮጵያ ለማፍሰስ ከወሰኑ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
የACCEM ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ዣኦ ዚቸን፣ ማኅበሩ እንደ አውሮፓያን ዘመን በ1987 የተቋቋመ፣ በቻይና በብሔራዊ ደረጃ ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል። ከ100 ሺህ በላይ የማምረቻ ድርጅቶችንና ከ2,600 በላይ ዩኒቨርሲቲዎችን በአባልነት እንደያዘም አብራርተዋል።
ማኅበሩ የንግድ ድርጅቶችንና የንግድ መሪዎችን በማገልገል፣ የንግድ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ ተወዳዳሪነትን ለማጠናከርና የቻይናን የንግድ ዘርፍ ልማት ለማበረታታት እንደሚሠራም ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ በኢንዱስትሪ አስተዳደር፣ በመረጃ ልውውጥ፣ በሙያ ሥልጠና፣ በኤግዚቢሽን አዘገጃጀት፣ በሕትመትና ስርጭት፣ በዓለም አቀፍ ትብብርና በማማከር አገልግሎቶች ዘርፎች እንደሚሳተፍ አስረድተዋል።
ወ/ሮ ዣኦ ዚቸን አክለውም፣ ACCEM በንግድ ድርጅቶች፣ በንግድ ሙያተኞችና በተዛማጅ ተቋማት መካከል የትብብርና የግንኙነት መድረክ ሆኖ እንደሚያገለግል ጠቁመዋል። ማኅበሩ የንግድ ዕውቀት ልውውጥን፣ የአስተዳደር ልምዶችን መጋራትን፣ የሙያ አቅም ግንባታንና በድርጅቶች መካከል የትብብር ግንኙነቶችን በማጠናከር ረገድ የሚኖረውን ሚናም አብራርተዋል።
ማኅበሩ ለንግድ ልማትና ለዓለም አቀፍ ትብብር ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ፣ ከቻይና ንግድ ድርጅቶችና ባለሀብቶች ጋር የንግድ ግንኙነት ለመመሥረት ለሚፈልጉ ተቋማት ጠቃሚ የትብብር አጋር ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል።
በውይይቱ የተነሱትን የትብብር ሀሳቦች ወደ ተግባር ለመቀየር፣ IPDC ከACCEM አመራሮችና ከማኅበሩ አባል ድርጅቶች ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክር የኮርፖሬሸኑ ዋናስራ አስፈጻሚ አቶ ፍጽም ከተማ ገልጸዋል። በተለይ የኮርፖሬሽኑ የኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ ስራን በማመቻቸት እና ፍላጎት ካላቸው የACCEM አባል ድርጅቶች ጋር B2B ስብሰባዎችን ቀጥተኛ ግንኙነት ለመፍጠርና ተጨባጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመለየት እንሰራለን ብለዋል።
ይህ ትብብር የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግርን ለማበረታታት እንዲሁም የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ልማት ለማፋጠን ጠቃሚ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
IPDC Chief Executive Holds Talks with ACCEM Delegation to Explore Chinese Investment Opportunities in Ethiopia
The Chief Executive Officer of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC), Mr. Fitsum Ketema, held discussions with a delegation led by Ms. Zhao Zichen, Secretary-General of the Association of China Commercial Enterprise Management (ACCEM), to explore investment opportunities and strengthen cooperation between the two institutions.
During the meeting, Mr. Fitsum highlighted IPDC’s role in accelerating Ethiopia’s industrial transformation by providing integrated industrial infrastructure and a conducive investment environment that enables investors to commence production within a short period.
He explained that IPDC is a government development enterprise responsible for administering 14 Special Economic Zones and industrial parks. He also reaffirmed the Corporation’s commitment to supporting ACCEM member companies interested in investing in Ethiopia by facilitating their engagement with available investment opportunities.
Ms. Zhao Zichen noted that ACCEM, established in 1987, is a national, non-profit social organization in China. She stated that the Association has more than 100,000 manufacturing enterprises and over 2,600 universities among its members.
She further explained that ACCEM promotes improved business management, enhanced competitiveness, and the development of China’s commercial sector. Its activities include industry management, information exchange, professional training, exhibitions, publications, consultancy services, and international cooperation.
Ms. Zhao emphasized that the Association serves as a platform for collaboration and communication among enterprises, business professionals, and relevant institutions. She highlighted its role in facilitating knowledge exchange, sharing management practices, strengthening professional capacity, and promoting cooperation among businesses.
The discussions highlighted ACCEM’s potential to serve as an institutional partner in connecting Chinese enterprises and investors with investment opportunities in Ethiopia, particularly within IPDC’s industrial parks and Special Economic Zones.
Mr. Fitsum reaffirmed IPDC’s commitment to strengthening engagement with ACCEM’s leadership and member enterprises. He noted that the Corporation would facilitate direct engagement with interested companies through business-to-business (B2B) meetings to identify concrete investment opportunities and support prospective investors.
The cooperation is expected to help attract Chinese investment to Ethiopia, promote technology and knowledge transfer, and contribute to the country’s industrial development and economic transformation.