ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሁለት ተጨማሪ ሹመቶችን ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች ሰጡ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ወ/ሮ ጃለኔ ሀሰንን የኮርፖሬሽኑ የፓርክ አስተዳደርና ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ወ/ሮ አመለወርቅ ብርሃኔ የኮርፖሬሽኑ ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርገው ሾሙ።
ወ/ሮ ጃለኔ ሀሰን ለአራት አመታት ኮርፖሬሽኑን በተለያዩ የአመራርና የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። በዚህም የኮርፖሬሽኑ ሰው ሀብት አመራር ምምሪያ ኃላፊ፣ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን አገልግለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ አቶ ፍጹም ከተማን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርገው መሾማቸው ይታወሳል።
አዲሱ ሹመት ኮርፖሬሽኑ አሁን ካለበት የዕድገት ደረጃ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንዲያሸጋግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
የሶስቱም ሹመት ከጥቅምት 12 ቀን ጀምሮ የተሰጠ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈ ቤት የወጣው ደብዳቤ ያመላክታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ይህንን ለማሳካት የሚያስችለውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ቀርጾ ባለፈው የበጀት ዓመት ወደ ሥራ ማስገባቱ ለአዲሱ አመራር የተሻለ መነሻና ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ይታመናል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሥሩ 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችንና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሚያስተዳድር ቁልፍ ብሔራዊ ተቋም ነው። ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን፣ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እየተወጣ ይገኛል።