አቶ ፍጹም ከተማ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ አቶ ፍጹም ከተማን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርገው ሾሙ።
ሽመቱ ከጥቅምት 12 ቀን ጀምሮ የተሰጠ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈ ቤት የወጣው ደብዳቤ ያመላክታል፡፡
አቶ ፍጹም ከተማ በኮርፖሬሽኑ ከ10 ዓመታት በላይ በተለያዩ የአመራርና የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።
በዚህም የሐዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ሥራ አስኪያጅ፣ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንዲሁም የፓርክ አስተዳደርና ኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሠርተዋል።
አቶ ፍጹም በተለያዩ የአመራር ደረጃዎች ባካበቱት ልምድ፣ ኮርፖሬሽኑን ከመሩ አምስት ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በተለያዩ ወቅቶች በመሥራት የተቋሙን የአሥር ዓመታት የለውጥ፣ የዕድገትና የተቋማዊ ሽግግር ሂደት በቅርበት የሚያውቁ አመራር ናቸው።
አዲሱ ሹመት ኮርፖሬሽኑ አሁን ካለበት የዕድገት ደረጃ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንዲያሸጋገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ኮርፖሬሽኑ ይህንን ለማሳካት የሚያስችለውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ቀርጾ ባለፈው የበጀት ዓመት ወደ ሥራ ማስገባቱ ለአዲሱ አመራር የተሻለ መነሻና ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ይታመናል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሥሩ 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችንና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሚያስተዳድር ቁልፍ ብሔራዊ ተቋም ነው። ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማፋጠን፣ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እየተወጣ ይገኛል።
Fitsum Ketema Appointed CEO of Ethiopia’s Industrial Parks Development Corporation
Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed has appointed Fitsum Ketema as Chief Executive Officer (CEO) of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC), entrusting him with leading one of the country’s key institutions responsible for advancing industrialization and investment.
The appointment is effective from October 22, 2026 onwards.
Fitsum brings more than a decade of experience at the Corporation, having served in various leadership and managerial positions. His previous roles include Manager of the Hawassa Special Economic Zone, Head of the Office of the CEO, and Deputy CEO for Park Administration and Operations Division.
Over the years, he has worked alongside five successive CEOs, gaining extensive institutional knowledge and firsthand experience of the Corporation’s transformation, growth, and organizational transition over the past decade.
His appointment is expected to help steer the Corporation into its next phase of development, building on the progress achieved to date and strengthening its contribution to Ethiopia’s industrial growth.
The Corporation has already developed a five-year strategic plan, which it began implementing in the previous fiscal year. The plan is expected to provide a strategic framework for the new leadership to advance the institution’s objectives and sustain its development momentum.
The IPDC is a key national institution mandated to manage 14 special economic zones and industrial parks across Ethiopia. It plays a central role in accelerating the country’s industrial transformation, attracting investment, and supporting sustainable economic growth.