በእንስሳት መኖ ምርትና ባዮቴክኖሎጂ ዘርፎች ለመስራት ፍላጎት ያላቸው የቻይና ባለሀብቶች ከኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጋር ተወያዩ
በእንስሳት መኖ ምርትና ባዮቴክኖሎጂ ዘርፎች ለመስራት ፍላጎት ያላቸው የቻይና ባለሀብቶች ከኮርፖሬሽኑ አመራሮች ጋር ተወያዩ
በእንስሳት መኖ ምርት፣ ባዮቴክኖሎጂና በግብርና ቴክኖሎጂ ዘርፎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ያላቸው ከ20 በላይ የቻይና ባለሀብቶች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር ተወያዩ።
በቻይናዋ ጓንግዚ ግዛት የእንስሳት መኖ አቀነባባሪዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሸን ሹይባኦ የመሩት የባለሀብቶች ልዑክ፣ ከተለያዩ የቻይና ግዛቶች የተውጣጡ ባለሀብቶችን፣ የንግድ አማካሪ ድርጅቶችን፣ በባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎችንና በግብርና ቴክኖሎጂ ልማት ላይ የሚሠሩ ተቋማትን የሚወክሉ ኃላፊዎችን አካቷል። ልዑኩ በአፍሪካ የመደበኛ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለመጀመር ሲያቅድ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ መዳረሻቸው መሆኗን ገልጿል።
የባለሀብቶቹን ልዑክ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ተወካይ አቶ ሚኪያስ ታደሰ ተቀብለው ያወያዩ ሲሆን፣ ኮርፖሬሽኑ ለባለሀብቶች ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች፣ ስለሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞኖችና የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም ስለሚገኙ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ገለጻ አድርገዋል።
ባለሀብቶቹ በኮርፖሬሽኑ በሚተዳደሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮችና ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞኖች ውስጥ ካፒታላቸውንና የቴክኖሎጂ ዕውቀታቸውን በማዋል ለመሥራት ከወሰኑ፣ መንግሥት ከታክስ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተለያዩ የማበረታቻ ሥርዓቶችን መዘርጋቱን ተወካዩ ገልጸዋል።
የኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በለጠ በበኩላቸው፣ ኮርፖሬሽኑ ለባለሀብቶች የተቀናጀ መሠረተ ልማትና የተለያዩ ድጋፎችን በማቅረብ በአጭር ጊዜ ወደ ምርት ሥራ እንዲገቡ ለማስቻል የተቋቋመ የመንግሥት የልማት ተቋም መሆኑን አስረድተዋል።
ባለሀብቶቹ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ወቅት መንግሥት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ መዋቅር ለመለወጥ የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን እያከናወነ ካለበት ወቅት ጋር የሚገጣጠም መሆኑንም አቶ ጳውሎስ ጠቁመዋል። ባለሀብቶቹ ለመሰማራት ያሰቡባቸው ዘርፎች በመንግሥት ትኩረት ከተሰጣቸው የኢኮኖሚ ክፍሎች መካከል የሚገኙ በመሆናቸው፣ ለኢንቨስትመንታቸው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት ብዛት ከዓለም ቀዳሚ ከሆኑ አምስት ሀገራት አንዷ መሆኗን ያስታወሱት አቶ ጳውሎስ፣ ሀገሪቱ ከዚህ ሀብት የምታገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እየሠራች መሆኑን አንስተዋል። በእንስሳት መኖ ምርትና በተያያዙ ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የእንስሳት ሀብቱን ምርታማነት ከማሳደግ ባለፈ፣ ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ እንደሚያግዝ አመላክተዋል። ይህም መንግስት የእስሳት ሀብቱ ዘርፍ ምርታማነት እዲያደግ የሚደርገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል ብለዋል፡፡
Chinese Investors Interested in Animal Feed Production, Biotechnology Hold Talks with IPDC Officials
More than 20 Chinese investors interested in investing in Ethiopia in the fields of animal feed production, biotechnology, and agricultural technology held discussions with officials of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC).
The delegation led by Shen Shuibao, President of the Guangxi Feed Industry Association, comprised investors from various Chinese provinces, representatives of business consulting firms, companies engaged in biotechnology, and officials from institutions working in agricultural technology development.
The delegation indicated that its first pre investment visits to Africa started in Ethiopia.
Mikiyas Tadesse, a representative of IPDC’s Investment Promotion and Marketing Division, received the delegation and briefed its members on the services provided by the corporation, the special economic zones and industrial parks under its administration, and the available investment opportunities.
He also explained that the Ethiopian government has established various tax-related progressive incentive schemes for investors who choose to invest their capital and technological expertise in industrial parks and special economic zones managed by the corporation.
Meanwhile, Pawlos Belete, Head of IPDC’s Corporate Communications Department, explained that the corporation was established as a government development institution to provide investors with integrated infrastructure and various support services, enabling them to commence production within a shorter period of time by reducing unnecessary bureaucratic red tape.
Pawlos noted that the delegation’s visit to Ethiopia came at a time when the government was undertaking various policy reforms aimed at transforming the country’s economic structure. He added that the sectors in which the investors intend to engage are among the priority areas identified by the government, a factor he said would help create a favorable environment for their investments.
Recalling that Ethiopia is among the world’s top five countries in terms of livestock population, Pawlos emphasized that the country is working to maximize the economic benefits derived from its livestock resources.
He further noted that investment in animal feed production and related technologies would not only improve livestock productivity but also help increase the economic benefits Ethiopia derives from the sector. He added that such investments would significantly support the government’s efforts to enhance productivity in the livestock sector.