• Striving for eco industrial park
logo

ከቻይናዋ ኒንቦ ከተማ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የጅማ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞን ጎበኙ

ከቻይናዋ ኒንቦ ከተማ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የጅማ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞን ጎበኙ

ከቻይና ዠጂያንግ ግዛት ኒንቦ ማዘጋጃ ቤት ሕዝብ ኮንግረስ ቋሚ ኮሚቴ የተውጣጡ ልዑካን ቡድን በጅማ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞን ጉብኝት በማድረግ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመቃኘትና በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የኢንዱስትሪ ትብብር ለማጠናከር ውይይት አድርገዋል።

በኒንቦ ማዘጋጃ ቤት ሕዝብ ኮንግረስ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ዳይሬክተር በአቶ ሁዋ ዌይ የተመራው ልዑካን ቡድን በሁለቱ ወገኖች መካከል የጋራ መግባባትን ለማጎልበት፣ ስትራቴጂካዊ አጋርነቶችን ለመፍጠርና በኢንቨስትመንት እና በኢንዱስትሪ ትብብር ዘርፎች ያሉ ዕድሎችን ለመለየት ያለመ ነው።

በጉብኝቱ ወቅት የጅማ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞን ሥራ አስኪያጅ የዞኑን የኢንዱስትሪ ልማት አቅምና በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መገጣጠም እና በሕክምና መሣሪያዎች ማምረት ዘርፎች ያሉ የትብብር ዕድሎችን አብራርተዋል። እንዲሁም በኢንዱስትሪ ልማትና በኢኮኖሚ እድገት ልምዷ ከምትታወቀው ከኒንቦ ከተማ ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር የጋራ ጥቅም የሚያስገኙ አጋርነቶችን ለመመሥረትና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉብኝቱ በጅማ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞን የቻይና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና የትብብር መስኮችን ለመለየት ዕድል ፈጥሯል። ይህ ተሳትፎ በተለይም በኢንዱስትሪ ልማት፣ በማምረቻ ዘርፍና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በማተኮር በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን ሰፊ የኢኮኖሚ ትብብር ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ከጅማ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ዞን ጉብኝት በተጨማሪ፣ የልዑካን ቡድኑ አባላት ጅማ ዩኒቨርሲቲንም ጎብኝተዋል። ይህም ከአካባቢው ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማስፋትና በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ዕድሎችን ለመመርመር ዕድል ፈጥሯል።

ይህ ጉብኝት ከኒንቦ ማዘጋጃ ቤት ተወካዮች ወደ ጅማ የተደረገው ሁለተኛው ይፋዊ ጉብኝት ሲሆን፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል እየተጠናከረ የመጣውን ግንኙነትና በኢኮኖሚ፣ በኢንዱስትሪና በተቋማዊ ትብብር ያላቸውን የጋራ ፍላጎት ያመለክታል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) እንደዚህ ያሉ ግንኙነቶችን በማጠናከር የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ዕድሎች ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማበረታታትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለመደገፍ እየሠራ ይገኛል።

 

Chinese Delegation from Ningbo Visits Jimma Special Economic Zone to Explore Investment Opportunities

A delegation from the Standing Committee of the Ningbo Municipal People's Congress of Zhejiang Province, China, has visited Jimma Special Economic Zone to explore investment opportunities and strengthen industrial cooperation between Ethiopia and China.

The delegation, led by Mr. Hua Wei, Deputy Director of the Standing Committee of the Ningbo Municipal People's Congress, comprised six representatives with expertise in legal affairs, budget administration, local governance, foreign affairs, and healthcare.

The visit aimed to foster mutual understanding, explore strategic partnerships, and identify potential areas of investment and industrial cooperation between Ningbo and Jimma.

During the visit, the manager of Jimma Special Economic Zone highlighted the zone's industrial development potential and opportunities for collaboration in agro-processing, electric vehicle assembly, and medical equipment manufacturing. The manager also emphasized the importance of strengthening engagement with Ningbo, a city known for its industrial development and economic achievements, to promote investment and establish mutually beneficial partnerships.

The visit provided an opportunity to discuss potential areas of cooperation and explore ways to encourage Chinese investment in Jimma Special Economic Zone. The engagement is expected to contribute to broader economic collaboration between Ethiopia and China, particularly in industrial development, manufacturing, and technology-related sectors.

In addition to visiting Jimma Special Economic Zone, members of the delegation also visited Jimma University, further expanding their engagement with local institutions and exploring opportunities for cooperation.

The visit marks the second official visit by representatives of Ningbo Municipality to Jimma, reflecting continued engagement between the two sides and their shared interest in strengthening economic, industrial, and institutional ties.

Through such engagements, the Industrial Parks Development Corporation (IPDC) continues to promote Ethiopia's industrial investment opportunities and encourage international partnerships that support industrialization, technology transfer, and sustainable economic development.