• Striving for eco industrial park
logo

የቻይና የንግድ ልዑክ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመመርመር ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን ጎበኘ

የቻይና የንግድ ልዑክ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመመርመር ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን ጎበኘ

ከቻይና ሄናን ግዛት የመጡ የግል ድርጅቶች ልዑካን ብድን አባላት በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ለማጠናከር እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመመርመር ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ጎብኝተዋል።

ልዑኩ የሄናን የግል ኢንተርፕራይዞች ማኅበርና የሹዋንፌይ ዓለም አቀፍ የንግድ አማካሪ ድርጅት (ሄናን) ኃ.የተ.የግ.ማ. ተወካዮችን ያካተተ ሲሆን፣ ጉብኝቱ የንግድ ግንኙነቶችን ለማስፋፋት፣ የኢንቨስትመንት አጋርነትን ለማጠናከር እና በቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎች የትብብር ዕድሎችን ለመለየት ያለመ ነው።

የሄናን የግል ኢንተርፕራይዞች ማኅበር ዋና ጸሐፊ አቶ ዋንግ ሎንግ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ማኅበሩ በሄናን ግዛት የሚገኙ የግል ድርጅቶችን የሚወክል ሲሆን፣ አባል ድርጅቶቹም በግንባታ፣ በአዲስ ኃይልና ሊቲየም ባትሪዎች፣ በአዳዲስ ቁሳቁሶች እና በሕንፃ ግንባታ ቁሳቁሶች ምርት ዘርፎች ይንቀሳቀሳሉ።

በጉብኝቱ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) አመራሮች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተሟላ መሠረተ ልማትና ለባለሀብቶች የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ለልዑኩ አብራርተዋል። በገለጻውም የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የፋብሪካ ሼድ ኪራይ፣ የለማ የኢንዱስትሪ መሬት፣ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች፣ የኢንቨስትመንት ጥበቃ ስምምነቶች እና ከሠራተኛ ግንኙነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተካተዋል።

ልዑኩ የቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን በመጎብኘት የመሠረተ ልማት አቅሙን፣ ያሉትን ተቋማትና ለወደፊት የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ሥራዎች ያለውን ምቹ ሁኔታ በቦታው ተመልክቷል።

ጉብኝቱ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል እየጠናከረ ከመጣው የኢኮኖሚና የንግድ ግንኙነት እንዲሁም በቤልት ኤንድ ሮድ ተነሳሽነት ሥር ከሚካሄደው ሰፊ የቻይናና የአፍሪካ ትብብር ጋር ተያይዞ የተካሄደ ነው።

ልዑኩ በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በአዲስ ኃይል፣ በማምረቻ ኢንዱስትሪና በሌሎች ዘርፎች ተግባራዊ የትብብር መስኮችን ለመለየት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። ይህም በሁለቱ አገራት መካከል የኢኮኖሚ እድገትን ለማጎልበትና ዘላቂ የንግድ አጋርነትን ለመመስረት እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ ለቻይናውያኑ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታና የኢንዱስትሪ ልማት ቅድሚያ የተሰጣቸውን ዘርፎች በቀጥታ እንዲገነዘቡ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ የመንግሥትና የግል ዘርፍ ተዋናዮች ጋር ሊኖሩ የሚችሉ የአጋርነት ዕድሎችንም ለመፈለግ ያግዛል።

ልዑኩ በሚቀጥሉት ቀናት ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መንግሥታዊ ተቋማት ጋር በመገናኘት የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችን፣ የቁጥጥር ማዕቀፎችንና ተጨማሪ የኢኮኖሚ ትብብር ዕድሎችን ለመወያየት ቀጠሮ ይዟል።

Chinese Business Delegation Visits Bole Lemi Special Economic Zone to Explore Investment Opportunities

A delegation of private enterprises from China's Henan Province has visited Bole Lemi Special Economic Zone in Ethiopia to explore investment opportunities and strengthen economic and trade cooperation between Ethiopia and China.

The delegation comprises representatives of the Henan Private Enterprises Association and Xuanfei International Business Consulting (Henan) Co., Ltd. The visit aims to promote business engagement, foster investment partnerships, and identify opportunities for collaboration across key economic sectors.

Speaking during the visit, Mr. Wang Long, Secretary-General of the Henan Private Enterprises Association, highlighted the association's broad private-sector representation in Henan Province, with member enterprises operating in industries including construction, new energy and lithium batteries, new materials, and building materials.

Leadership of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC) briefed the delegation on the integrated infrastructure and investment services available in Ethiopia's industrial parks. The briefing covered one-stop services, factory shed rentals, developed industrial land, utilities, investment incentives, investment protection agreements, and labor-related matters.

During the visit, the delegation toured Bole Lemi Special Economic Zone to assess its infrastructure, facilities, and overall business environment for potential investment and industrial operations.

The visit comes amid growing economic and trade ties between Ethiopia and China, as well as expanding China-Africa cooperation under the Belt and Road Initiative.

The delegation expressed interest in exploring practical areas of cooperation in infrastructure development, new energy, manufacturing, and other sectors, with the aim of supporting bilateral economic growth and establishing long-term business partnerships.

The visit provides an opportunity for the Chinese enterprises to gain first-hand insight into Ethiopia's investment climate and industrial development priorities while exploring potential partnerships with Ethiopian public and private-sector stakeholders.

The delegation is also scheduled to meet with relevant Ethiopian government institutions in the coming days to discuss investment policies, regulatory frameworks, and further opportunities for economic cooperation.