• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month, 2 weeks ago
  • 113 Views

ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ

"የአካባቢውን የተፈጥሮ  ሀብት ያማከለ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር እንሰራለን" ዶክተር ፍስሃ ይታገሱ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ በጅማ  ኢንዱስትሪ ፓርክ የአካባቢውን የተፈጥሮ እምቅ አቅም ያማከለ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር የሚያስችሉ  ስራዎች እንደሚሰሩ ገለፁ። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት የጅማ  ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ፤ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር የተፈጠረውን የገበያ ትስስር ፤ ተረፈ ምርትን ወደ ሀብት የመቀየር ስራን ጨምሮ  እንዲሁም አጠቃላይ የፓርኩን ወቅታዊ ሁኔታ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው  በኢንዱስትሪ ፓርኩ ያሉ አምራች ኩባንያዎች ስላሉበት የምርት እንቅስቃሴ ፤ የስራ እድል ፈጠራ ፤ ኤክስፖርት እና የተኪ ምርት ተግባራት ላይ ከባለሃብቶቹ ጋር የተወያዩ ሲሆን በቀጣይም በኢንዱስትሪ ፓርኩ መሰራት የሚገባቸው አበይት ጉዳዮች ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። 

ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለኢንቨስተሮች ያለው ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለመሰማራት  በአካባቢው ያለው የተፈጥሮ እምቅ አቅም ምቹ መሆኑን ዶክተር ፍስሃ ጨምረው  ገልፀዋል። 

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ከነበረው የጉብኝት ፕሮግራም ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርም ተከናውኗል።