• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month, 2 weeks ago
  • 105 Views

የቻይናውያን ባለሀብቶች እይታ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች  የተመለከትናቸው የኢንቨስትመንት መሰረተ ልማቶች ለትርፋማ ኢንቨስትመንት መሰረት ናቸው፡፡ - ቻይናውያን ባለሀብቶች 

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ  ያሉት የኢንቨስትመንት አማራጮችና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆናቸውን የቻይና ከፍተኛ የመንግስትና የቢዝነስ የልዑካን  ቡድን አባላት ገለፁ። 

ከ90 በላይ ከቻይና የተለያየ ግዛት የመጡ ከፍተኛ የመንግስትና የቢዝነስ የልዑካን ቡድን አባላት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴንና አጠቃላይ የምርት ሂደትን ጎብኝተዋል። 

የልዑካን ቡድኑ አባላት በፓርኩ  በነበራቸው ጉብኝት በኢንዱስትሪ ፓርኩ ስላለ አጠቃላይ የመሰረተ ልማት አቅርቦት፤የኢንቨስትመንት አማራጮችና በፓርኩ ኢንቨስት ያደረጉ ባለሃብቶችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ  በፓርኩ ስራ አስኪያጅ ትንሳኤ ይማም ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት  በኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለው የመሰረተ ልማትና የኢንቨስትመንት አማራጭ  ምቹና ሳቢ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ገብተው  ለመስራት የቅድመ ኢንቨስትመንት  ስራዎችን እንደሚያከናውኑ አሳውቀዋል። 

ኢትዮጵያ እና ቻይና በንግድ እና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ፤እንዲሁም ከ90 በላይ ከተለያዩ የቻይና ግዛቶች የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት እና የቢዝነስ ልዑካን ቡድንን ያሳተፈ የኢትዮ-ቻይና ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡