• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month, 2 weeks ago
  • 103 Views

የኢትዮ-ቻይና አመታዊ ቢዝነስ

"በኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል "- ዶክተር ፍሰሃ ይታገሱ

 በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና  የቻይና ባለሀብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት  እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለፁ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት ከ90 በላይ ቻይናውያን ባለሀብቶችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት አመታዊው የኢትዮ-ቻይና ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው።

ዋና ስራ አስፈጻሚው  በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በመላው ሃገሪቱ ደረጃቸውን ጠብቀዉ በተገነቡት ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የነፃ የንግድ ቀጠና የቻይናውያን ባለሀብቶች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው አሁንም ተሳትፏቸውን ይበልጡን ለማሳደግ የሚያስችል ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙን መሰረት ያደረገ ተቋማዊ ሪፎርም መተግበራቸውን ገልፀዋል።

በመላው ሀገሪቱ በተገነቡት 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና እና ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የመሰረተ ልማት ፤  አንድ ማዕከል አገልግሎትና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች እንዲሁም የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ዶ/ር ፍስሃ በፎረሙ አብራርተዋል።
 
የኢትዮ-ቻይና ቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያ እና ቻይና በንግድ እና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ሲሆን በፎረሙ  የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ፤እንዲሁም ከተለያዩ የቻይና ግዛቶች የተውጣጡ ከፍተኛ የመንግስት እና የቢዝነስ ልዑካን ተሳትፈውበታል።

ከ90 በላይ ቻይናውያን ባለሀብቶችን የያዘዉ ልዑካን ቡድን በነገዉ እለት በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመስክ ጉብኝት የሚያደርግ ይሆናል ።