• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month, 2 weeks ago
  • 170 Views

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ መጀመር

"የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ስራ ተመልሷል" - አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ምርት ሂደት መመለሱን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

በሰሜኑ ግጭት ምክንያት ላለፉት ግዜያት ስራ አቁሞ የቆየው የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮርፖሬሽኑ ባደረገው ከፍተኛ የርብርብ ስራና በተሰጠው ትኩረት ዛሬ ወደ ስራ መግባቱን ነው ዋና ስራ አስፈፃሚው የገለፁት።

ከዚህ በመቀጠልም በፊት በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ያመርቱ የነበሩ ኩባንያዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እንዲሁም አዳዲስ ኢንቨስተሮች በፓርኩ ለማምረት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የቅድመ ኢንቨስትመንት ስራዎቻቸውን እያጠናቀቁ መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ኮርፖሬሽኑም ኩባንያዎቹ ወደ ምርት ሂደት እንዲገቡ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ አሁንም ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባ፤ ውጤታማነቱ ከፍ እንዲል እንዲሁም ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ለመፍጠር እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅርበት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።

የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ238 ሄክታር መሬት ላይ ተገንብቶ በ2017 (እ.አ.አ) ስራ የጀመረ ሲሆን 15 የማምረቻ ሼዶች እንዲሁም የለማ መሬት ለኢንቨስተሮች ዝግጁ ተደርጓል።