• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month, 4 weeks ago
  • 155 Views

በሩሲያ የኖቭግሮድ ግዛት ከፍተኛ ኃላፊዎች

በሩሲያ የኖቭግሮድ ግዛት ከፍተኛ ኃላፊዎች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ የራሺያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ቴሬሂን በተገኙበት በሩሲያ የኖቭግሮድ ግዛት ቀዳሚ ምክትል ገዢና አስተዳዳሪ ቦግዳኖቭ ኢቭጌኒ የተመራ ልዑክ ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል። 

በውይይቱም ዋና ስራ አስፈፃሚው ኮርፖሬሽኑ ሲያከናውናቸው የቆዩ እና እያከናወናቸው የሚገኙ ኢንቨስትመንት ተኮር ዝርዝር ተግባራት ለልዑክ ቡድኑ ያብራሩ ሲሆን ኢትዮጵያና ሩሲያ ያላቸው የረጅም ግዜ ፅኑ ግንኙነት በኢንቨስትመንት ለማጠናከር እንደሀገር ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን አስረድተዋል። 

የልዑክ ቡድኑ መሪ ቦድጋኖቭ ኢቭጌኒ ከልዑካቸው ጋር ኢትዮጵያ ሲመጡ ባዩት አቀባበልና ከባቢ ደስ መሰኘታቸውን ገልፀው በኖቭጎሮድ ግዛት የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ለማድረግ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል። 

ልዑክ ቡድኑ ከኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ካደረገው ውይይት በተጨማሪ የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ከኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ካሚል ኢብራሂም ጋር ተዟዙረው ተመልክተዋል። በምልከታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። 

ኮርፖሬሽኑ በሩሲያ ያለውን ሰፊ ገበያና የኢንቨስትመንት አቅም በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ዉስጥ ለመጠቀም እንዲሁም በፓርኩ ዉስጥ ያሉ አምራቾች የሩሲያን ሰፊ ገበያ መጠቀም እንዲችሉ በኢትዮጵያ ከሩሲያ ኤምባሲ ጋር በቅንጅት ለመስራት መስማማቱ የሚታወስ ነው። 

Senior officials of Russian Novgorod region expressed their interest in working together with IPDC 

Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse had a discussion with a delegation led by the first deputy governor and administrator of Russia's Novgorod region, Bogdanov Evgenii, in the presence of Russian Ambassador to Ethiopia Evgeni Terehin. 

During the discussion, Mr. Aklilu explained to the delegation the investment-oriented activities that the corporation has been carrying out and is currently doing, and explained that there is a strong desire as a country to strengthen the long-term relationship between Ethiopia and Russia through investment. 

The leader of the delegation, Bodganov Evgeny, expressed his happiness with the welcome and atmosphere he and his delegation saw when they came to Ethiopia and announced that they will work to bring industries and manufacturers from Novgorod region to Ethiopia. 

In addition to the discussion with IPDC CEO Aklilu, the delegation toured the entire operation of Kilinto Industrial Park with Kamil Ibrahim, Deputy CEO of the operations sector of the corporation. And They expressed that they are happy with their observation. 

It is to be remembered that the corporation has agreed to work in coordination with the Russian Embassy in Ethiopia to use the investment potential of Russia in the industrial parks and Dire Dawa Free Trade zone that it manages, as well as for the manufacturers in the park to be able to use the vast market of Russia.

#invest_in_zero_waiting_time_bureaucracy