• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 3 weeks ago
  • 280 Views

የተወዳዳሪነትና የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት

የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የተወዳዳሪነት አቅምን ለማሳደግ የዓለም ባንክ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ይህን የገለጸው በዓለም ባንክ ድጋፍ ባለፉት ስምንት ዓመታት በቦሌ ለሚ ሁለት እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሲተገበር የቆየው የተወዳዳሪነትና የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት የመዝጊያ ፕሮግራም ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ ነው።

በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ፕሮጀክቱ በቦሌ ለሚ ሁለት እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከ10ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣት ዜጎች የስራ እድሎችን ከመፍጠር በተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግ በኩል አዎንታዊ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።

አቶ አክሊሉ ፕሮጀክቱ ላለፉት ስምንት ዓመታት በርካታ ውጣውረዶችን ማለፉን አስታውሰው በዚህ ሂደት ውሰጥ ፕሮጀክቱ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ እና በውጤቱም የሀገርን እድገትና ልማት እንዲደግፍ ለማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የተወዳዳሪነትና የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ዓለም ባንክ ባደረገው የ425 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ባለፉት ስምንት ዓመታት በቦሌ ለሚ ሁለት እና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተሰሩ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በተጨማሪ ከ10,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ በፕሮጀክቱ ትግባራ ላይ ለተሳተፉ ባለድርሻ አካላት እና ተቋማት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

'World Bank support has been vital in increasing citizens’ competitiveness and equity' - Aklilu Tadesse, IPDC CEO

Industrial Park Development Corporation has announced that World Bank support has been vital in ensuring citizen equity and competitiveness.

The announcement was made by Aklilu Tadesse, IPDC CEO in a closing ceremony of Competitiveness and Job Creation Project ( CJC ) of the World Bank.

The CJC project of the World Bank in Ethiopia has been operational in the past eight years with a total project cost of 425 million USD.

IPDC CEO, Akililu Tadesse, stated that the project has created more than 10 thousand job opportunity for citizens apart from securing hard currency to the country while addressing the guests present at the grand closing ceremony held at Radisson Blue Hotel, Addis Abeba today.

In his statement, the CEO acknowledged the management, employees and stakeholders who helped to realize the project objectives during its implementation phase.

And he expressed his team readiness to work with the global financial body in the future.

CJC project was effective in developing Bole Lemi Industry Park Phase Two and Kilinto Industry Park horizontal infrastructural development apart from creating 10 thousand job opportunity to citizens.

#Worldbank