• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months ago
  • 394 Views

5ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር

በመጪው ክረምት ከ1 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው

ኮርፖሬሽኑ በ5ኛው ዙር የአረንጓዴ አሸራ መርሀ ግብር ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው 11 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና በ5ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የተለያየ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሰራዎችን በመከናወን ላይ ይገኛሉ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ የ2015 በጀት ዓመት 9ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በጅማ ከተማ ሲካሄድ ካስተላለፉት ዋና ዋና የስራ መመሪያዎች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን አጠናክሮ ማስቀጠል አንዱ እንደሆ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠናው የኮርፖሬሽኑን ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት የማቅረብ ስራዎችን እንዲሰራና በተለይም እንደየአካባቢው የአየር ንብረት ሁኔታ ተስማሚና ለምግብነት የሚዉሉ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ፍራፍሬ አብቃይ ችግኞች እንዲተከሉ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፉት 4 ዙሮች በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ2 ሚሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የጽድቀት መጠናቸውም ከ90 በመቶ በላይ መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ አካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

#GreenLegacy