ባለፉት 9 ወራት ከውጭ ንግድ ኤክስፖርት ከ121.9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማግኘት መቻሉ ተገለጸ፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን በጅማ ከተማ በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ወደ ውጭ ምርቶችን በመላክ ለማግኘት ካቀደው 156 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ውስጥ ከ 121 ሚሊዮን 914 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ማግኘት መቻሉ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 9 ወራት ተኪ ምርትን በማምረት ረገድ በቦሌ ለሚ፣ በደብረብርሀን እና ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቻ ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ዘላቂ የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉም በመድረኩ በማሳያነት ተነስቷል።
ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ከሚገኙባቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የግብርና ምርምር ማዕከላት ጋር በመቀናጀት በተሰራው ስራ ለአካባቢው አርሶ አደሮች ዘላቂ የገበያ ትስስር መፍጠር ከመቻሉም ባለፈ የምርጥ ዘር አቅርቦት፣ የክህሎት፣የስልጠና እና የምክር ድጋፍ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ውጤቶች መመዝገባቸውን በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በ9 ወራቱ ብቻ ከ36,800 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡
It was announced that in the last 9 months, IPDC has been able to earn more than 121.9 million USD from foreign trade exports.
Industrial Parks Development Corporation is reviewing the 2015 fiscal year 9 months plan performance in Jimma City.
It was stated in the forum that the corporation has managed to get 121.9 million USD out of the 156 million US dollars that it planned to earn by exporting products.
In terms of import substitution, IPDC has been able to create sustainable market links for more than 100,000 farmers in only Bole Lemi, Debre Birhan and Jimma Industrial Parks in the last 9 months. IPDC's ffective coordination with the universities and agricultural research centers where the industrial parks are located enabled farmers to create sustainable market links, and also got the best seed supply, skills and additional advisory services.
On the other hand, it is stated that more than 36,800 citizens have got job opportunities in 11 industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone.