• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 12 months ago
  • 252 Views

የኮርፖሬሽኑ ስኬት በተኪ ምርት

ባለፉት 9 ወራት ተኪ ምርት በማምረት ከ 129 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለፀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በጅማ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ኮርፖሬሽኑ በሪፖርቱ ባለፉት 9 ወራት ለሀገር ውስጥ ገበያ የተለያዩ ምርቶችን በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ጫናን ከመቀነስ /Import subsitiution/ አኳያ ከ125 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለማዳን አቅዶ ከ 129 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በማዳን የእቅዱን ከ100% በላይ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል።

ለዉጤቱ መመዝገብ ባለፉት ወራት የኮርፖሬሽኑን አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም በማድረግና ከባለድርሻ አካላት ጋር ይበልጡን በመቀራረብ በተሰራው ከፍተኛ የንቅናቄ ስራ መሆኑን በመድረኩ ተነስቷል።

በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት 9 ወራት ብቻ ከወጪ ንግድ ( ኤክስፖርት ) ከ121 ሚሊዮን 934 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ማግኘት መቻሉን በሪፖርቱ ተብራርቷል።

ኮርፖሬሽኑ የባለፉት 9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን በመገምገም ላይ ሲሆን በግምገማው የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከርና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ በቀጣይ 3 ወራት በትብብር ለመስራት የሚያስችል አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል።

In the last 9 months, it was revealed that more than 129 million dollars was saved by import substitution

IPDC's 2015 fiscal year 9 months plan performance report evaluation is being held in Jimma city.

In the report, the corporation planned to save more than 125 million US dollars by providing various products to the local market in the last 9 months from reducing the pressure of foreign currency /Import substitution/ and it was stated that IPDC was able to achieve more than 100% of the plan by saving more than 129 million US dollars.

It was brought up in the forum that the result was registered in the past months by reforming the service delivery of the corporation and the great mobilization work done in cooperation with the stakeholders.

On the other hand, IPDC has earned more than 121 million 934 thousand USD from exports in only 9 months of 2015 fiscal year.

IPDC is evaluating the performance report of the last 9 months and it is expected to strengthen the achievements recorded in the evaluation and set directions for working together on the challenges in the next 3 months.