• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 9 months ago
  • 899 Views

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና በቻይና የኢትዮጵያ ኢምባሲ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ተፈራ ደርበው እና የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ተወያይተዋል 

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ቻይና ያላቸውን የኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማጠናከር ፤ የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት በሰፊው ማስተዋወቅ ፤በዋነኛነት ደግሞ የቻይና አምራች ኩባንያዎችና ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው ማምረት በሚችሉባቸው ሁኔታዎችና መሰል ሊከወኑ በሚገባቸው ዝርዝር ስራዎች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በውይይቱ ወቅት በኮርፖሬሽኑ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎች እና የኢንቨስትመንት ፍሰት ዙሪያ ለአምባሳደሩ ዝርዝር መረጃ የሰጡ ሲሆን አምባሳደር ተፈራም የሪፎርም ስራዎቹን  አበረታችና ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አንስተዉ  በጋራ በመስራት ውጤት ለማስመዝገብ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል። ለዚህም መላው የኤምባሲው አመራርና ፈፃሚ ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል ።

ውይይቱን መሰረት በማድረግም በቀጣይ በእቅድ ተይዘው መከናወን የሚገባቸው ጉዳዮች የተለዩ ሲሆን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉ ምቹ ኢንቨስትመንት አማራጮችንና ማበረታቻዎችን  በቻይና ሀገር የማስተዋወቅ ፤  እንዲሁም የተጀመረውን ግንኙነት የሚያጠናክሩ አሰራሮችን ተግባራዊ ለማድረግም ከስምምነት ተድርሷል። 

Aklilu Tadesse, Chief Executive Officer of Industrial Parks Development Corporation, had an online discussion with H.E. Ambassador Tefera Deribew,  Extraordinary & Plenipotentiary Ambassador of the Federal Democratic Republic of Ethiopia to the People's Republic of China and his team.

During their discussion, they exchanged views on the issue of strengthening the investment and economic ties between Ethiopia and China, promoting Ethiopian investment widely, and mainly on the conditions under which Chinese manufacturing companies and investors can enter and produce in industrial parks and the detailed work that should be done. 

IPDC CEO, Aklilu Tadesse gave detailed information to the ambassador about the reform works and investment flow being carried out by the corporation. Ambassador Tefera praised the reform works of IPDC pointed out that they are encouraging. 

Based on the discussion, issues that need to be planned in the future have been identified and an agreement has been reached to promote investment in China, find investors and show investment options and incentives in industrial parks, as well as to implement procedures that strengthen the relationship.