• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 9 months ago
  • 834 Views

የጅቡቲ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

በጅቡቲ የንግድ ሞክር ቤት ፕሬዚዳንት የተከበሩ የሱፍ ሙሳ ዳዋሌህ የተመራ ልዑካን ቡድን የቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝቷል።

የልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ በቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተከናወኑ የልማት ስራዎችንና የባለሀብቶችን እንቅስቃሴ የጎበኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በስራ እድል ፈጠራ፣ የኢንቨትመንት አማራጭ እና ለባለሀብቶች ስለሚደረጉ ማበረታቻዎች፣ እና በቴክኖሎጅ ሽግግር ላይ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የልዑካን ቡድኑን የተቀበሉት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን የንግድ ምክር ቤት ልዑካን ቡድኑ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መጎብኘታቸው በሁለቱ ሀገራት ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር የሚያጠናክር ከመሆኑ በተጨማሪ ከጅቡቲ በቅርብ ርቀት በተገነባው የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የጅቡቲ ባለሀብቶች ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡

የጅቡቲ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሱፍ ሙሳ ዳዋሌህ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እና አማራጭ በጅቡቲ የሚገኙ ባለሃብቶችን ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸው በተለይም የጅቡቲ ባለሀብቶች በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ገብተው እንዲሰሩ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።

የጅቡቲ የንግድ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን አባላቱ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲን የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከርና ለማስተዋወቅ ያለመ ጉብኝት በኢትዮጵያ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።