#የምትተክል_ሃገር_የሚያፀና_ትውልድ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዋናው መስሪያ ቤትና በአዲስ አበባ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አመራርና ሰራተኞች ፤ ባለሀብቶች ፤ የፀጥታ አካላት እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ የ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካሂደዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው 12 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና 1 ነጻ የንግድ ቀጠና ውስጥ ለ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ በሁሉም የኢንቨስትመንት ማዕከሎች የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሃ ይታገሱ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት መካሄዱ ይታወሳል፡፡