• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months ago
  • 221 Views

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) በይፋ የከፈቱት የጤና ኤግዚቢሽን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) የጤና ኤግዚቢሽንን መርቀው ከፈቱ 

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) በኤግዚቢሽን ማዕከል የተዘጋጀውንና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚሳተፍበትን "ጤናችን በምርታችን" ኤግዚቢሽን መርቀው ከፍተዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዐቶችንና እና መድኃኒቶችን ለማምረት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ከማድረግ ጀምሮ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን ገልፀው ከ120 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ላላት ኢትዮጵያ መድኃኒቶችን በራስ ዐቅም ማምረት ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም ብለዋል። 

በኤግዚቢሽኑ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ የሚያስተዳድረው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለታዳሚዎች እይታ የቀረበ ሲሆን በፓርኩ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች ፤ አምራች ኩባንያዎች እና የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሁም ወቅታዊ የፓርኩ እንቅስቃሴ ለጎብኚዎች ቀርበዋል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጤና እና ጤና ነክ መድሀኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶችና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ በማሰብ እና ለዚሁ ተብሎ የሚወጣን የውጪ ምንዛሪ ለማዳን ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመገንባት ለሀገር በቀል እና አለም አቀፍ አምራቾች አቅርቧል። 

በኤግዚቢሽኑ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድረው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ እያመረቱ የሚገኙ ኩባንያዎችን ጨምሮ ከ130 በላይ የዘርፉ አምራቾች ፤ ከ50 በላይ አለም አቀፍ የቢዝነስ ጎብኚዎች የሚሳተፉ ሲሆን ከ100 ሺህ በላይ ጎብኚዎችም ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአለም ዓቀፍ ደረጃ አስፈላጊ የሚባሉ መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ በ279 ሄክታር መሬት ላይ በአዲስ አበባ የገነባው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአፍሪካ ለፋርማሲዩቲካል ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ታስቦ የተገነባ ብቸኛው ኢንዱስትሪ ፓርክ ነው። 

#Invest_in_Zero_Waiting_bureaucracy