• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months ago
  • 231 Views

መሬታችን ለባለሀብቶቻችን

"ኢትዮጵያውያን አምራቾች በማኑፋክቸሪንግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማድረግ አላማን ሰንቀን እየሰራን ነው" አክሊሉ ታደሰ

ኢትዮጵያዊያን ኢንዱስትሪያሊስቶችን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ብቁና በአለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የማድረግ ትልቅ ራዕይ ሰንቀን እየሰራን ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ገለጹ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን መልዕክት ያስተላለፉት “መሬታችንን  በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶቻችን” በሚል መሪ ቃል ለ2 ወራት የሚቆይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ የለሙ መሬቶችን በሃገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በስፋት ለማስያዝ ያለመ የንቅናቄ መድረክ መጀመርን አስመልክቶ በኦፊሲኤላዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

አቶ አክሊሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ኢትዮጵያውያን "ጊዜው አሁን ነዉ ፤ ነገ ይረፍዳል " በሚል ርዕስ ባስተላለፉት  መልዕክት ባለፉት አምስት አመታት መንግስት አስቻይ መደላድሎችን ለመፍጠር  የተገበራቸውን በርካታ የሪፎርም ስራዎች መሰረት በማድረግ በኮርፖሬሽን ደረጃ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ የነፃ ንግድ ቀጠና ያለውን የአገር ዉስጥ ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በርካታ የሪፎርም ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

በኮርፖሬሽኑ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ለማበረታታት የተተገበረው ሪፎርም ከባለፉት ሁለት አመታት ወዲህ የአገር ዉስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ ከነበረበት ከ10 በመቶ በታች አሁን ላይ 55 በመቶ መድረሱንና ይህን አበረታች አፈፃፀም በመጪዎቹ 2 ወራት ለማሳደግ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ በትናንትናው ዕለት መጀመሩን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አሳውቀዋል፡፡

አቶ አክሊሉ በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተቀመጠውን አቅጣጫ ተግባራዊ በማድረግ  ወጣት ጀማሪዎችን እና የማምረቻ ቦታ ያጡ ኢትዮጵያዊ አምራቾችን ለመደገፍና ይበልጡን ለማበረታታት ከ 70 በላይ የሚደርሱ የአገር ዉስጥ ባለሀብቶችን በመጀመሪያ ዙር በማሳተፍ በቦሌ ለሚና ቂሊንጦ ፓርኮች ንቅናቄ ማስጀመራቸውንና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ፤ ልምድና ክህሎት ያላቸው በሙሉ የዚህ ልዩ አጋጣሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ   ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።