የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ መሪዎች በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን 3ኛውን "ኢትዮጵያ ታምር ት” ኤክስፖ ጎብኝተዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን ኑሮ ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከሉን በዛሬው እለት አስጀምሯል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሸን በኩል የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሃብቶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል የመሰረተ ልማት ዝግጁነት ቢኖርም የተለያዩ ዘርፎችን ያማከለ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በቅንጅት መሰጠት ካልተቻለ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳደግ እንደማይቻል የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር ) ገለጹ፡፡