• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 4 months ago
  • 382 Views

በዩናይትድ ኪንግደም የተጀመረው ከታሪፍ ነፃ ገበያ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ባለሀብቶች በዩናይትድ ኪንግደም ከታሪፍ ነፃ ገበያ ምርቶቻቸውን ለማቅረብ የሚያስችል የታዳጊ ሀገራት ነፃ ንግድ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ

የታዳጊ ሀገራት አምራቾች በዩናይትድ ኪንግደም ገበያ ምርቶቻቸውን ከታሪፍ ነፃ እንዲያቀርቡ የሚያስችል የመክፈቻ መርሃ ግብር በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የተገኙት የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስቴር ናይጄል ሀድልስተን የታዳጊ ሀገራት ነፃ የንግድ ፕሮግራም በ65 የዓለም ሀገራትና በ37 የአፍሪካ ሀገራት የሚጀመር መሆኑን ገልፀው በኢትዮጵያ በአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም በሌሎች የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ምርት የተሰማሩ አምራቾች በዩናይትድ ኪንግደም ገበያ ላይ ምርቶቻቸውን በነፃ እንዲያቀርቡ ያግዛል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከአጎዋ እድል መሰረዝ ጋር ተያይዞ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ባለሀብቶች ያለባቸውን የገበያ ችግር ለመቅረፍ ኮርፖሬሽኑ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የገበያ አማራጮችን ሲያፈላልግ መቆየቱን ገልፀው የዛሬው የታሪፍ ነፃ የንግድ ፕሮግራም የገበያ ማፈላለጉ አንድ አካል ነው ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሚሰሩ ባለሀብቶች ገበያ ማፈላለግ ምንም እንኳን የኮርፖሬሽኑ ኃላፊነት ባይሆንም ይህ አጋጣሚ ለኢንቨስተሮቻችን ምቹ ሁኔታ ለማመቻቸት እና የሀገርን እድገት ለማስቀጠል የተሰራው ስራ ውጤት ማሳያ መሆኑንና ሌሎች የገበያ መዳረሻዎች በሂደት ላይ እንደሚገኙ ማሳያ መሆኑን አቶ አክሊሉ ጨምረው ገልጸዋል።

ከታሪፍ ነፃ የንግድ ፕሮግራሙ በ65 ሀገራት የሚኖሩ ከ3 ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግና ከ20 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ምርቶችን በዩናይትድ ኪንግደም ገበያ በነፃ እንዲያቀርቡ የሚያግዝ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል ።

Tariff free trade launch program for developing countries was held to allow investors manufacturing in industrial parks to supply their products to the UK tariff-free market.

Inauguration program was held at Bole Lemi Industrial Park to allow manufacturers from developing countries to supply their products to the UK market Tariff-free.

Nigel Huddleston of the United Kingdom Ministry of Commerce, who was present at the opening of the program, said that the trade program for developing countries will start in 65 countries of the world and 37 African countries. He added that it will help the manufacturers engaged in the production of garment, textiles and other manufacturing sectors in Ethiopia to supply their products to the UK market for free.

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, said that the corporation has been searching for market options in cooperation with other stakeholders to address the market problems faced by investors working in industrial parks in connection with the cancellation of AGOA.

Mr. Aklilu added that, although it is not the corporation's responsibility to find a market for investors working in industrial parks, this opportunity is a demonstration of the results of the work done to facilitate a comfortable environment for investors and to continue the country's development, and also to get other market destinations which are in the process.