• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 6 months ago
  • 784 Views

የኮርፖሬሽኑ ልዑክ በቻይና

የኮርፖሬሽኑ ልዑክ በቻይና ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተመራ ልዑክ ቡድን በቻይና ይፋዊ የስራ ጉብኝ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማርኬቲንግ እና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ከሌሎች የኮርፖሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች ጋር በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በጉብኝቱ ቻይናውያን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ይበልጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማስቻል አጠቃላይ የመንግስት የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራዎች ላይ እና በአገሪቱ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን አስመልክቶ መረጃ የመስጠት ብሎም ከባለሀብቶች ጋር የተናጠል ዉይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የኮርፖሬሽኑ ልዑክ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያካሄደ ሲሆን በቻይና ከኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተፈራ ደርበው ጋር ስለ ኢንቨስትመንት ምልመላ ስራዎች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዉይይት ተካሂዷል።

የኮርፖሬሽኑ የማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊው አቶ ዘመን ጁነዲንና የልዑካን ቡድኑ ስለኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ የሪፎርም ተግባራትና የስራ እንቅስቃሴ፣ የዉጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ባለፉት 9 ወራት የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶችን እና ለኢንቨስተሮች የተዘጋጁ ምቹ ሁኔታዎችን አስመልክተው መረጃ ሰጥተዋል። ከኤምባሲው ጋር ከወራት በፊት የተጀመሩ ፍሬያማ ስራዎችም ይበልጥ ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል።

ልዑኩ በቆይታው በቻይማ የተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን፣ ነፃ የንግድ ቀጠናዎችን እና የኢንቨስትመንት ቦታዎችን የሚጎበኝ ይሆናል ።

IPDC delegates are making an official visit in China

Marketing and Communication Department of Industrial Parks Development Corporation is on an official visit to Beijing, the capital of China, along with other officials of the corporation.

The delegation of the corporation made an official visit to the Ethiopian Embassy in China and a discussion was held with the Ethiopian Ambassador to China. H.E Tefera Derbew about the investment recruitment process.

During the visit, to enable Chinese investors to invest in Ethiopia's industrial parks, they delegates are providing information on the government's economic reforms and favorable investment conditions, as well as separate discussions with investors.

The delegation of the corporation made an official visit to the Ethiopian Embassy in China and a discussion was held with the Ethiopian Ambassador to china H.E Tefera Derbe about the investment recruitment process.

The head of IPDC's marketing and communication department, Mr. Zemen Junedin, gave detailed information about the corporation's general activities, preparations made to attract foreign investment and favorable conditions for investors.

Consultations were held on the issues of continuing the fruitful activities that have been started with the embassy.