ኮርፖሬሽኑ ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ካስመዘገቡ ኩባንያዎች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ካስመዘገቡ 10 ሀገር በቀል ኩባንያዎች ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል።
የውል ስምምነቱን የተፈራረሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የኩባንያዎቹ ተወካዮች ናቸው።
የውል ስምምነቱ አስሩ ኩባንያዎች በቦሌ ለሚ፣ በቂሊንጦ፣ በሰመራ፣ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በ ነፃ ንግድ ቀጠና በኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ሲሆን በአጠቃላይ ከ7 ሺ 400 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥሩ ይሆናል።
ኩባንያዎቹ በተጠቀሱት ኢንዱስትሪ ፓርኮች መሰረተ ልማት የተሟላላቸው የማምረቻ ሼዶችን እና የለማ መሬት የሚረከቡ ሲሆን በአጠረ ግዜ ወደ ምርት ሂደት ይሸጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
IPDC has signed contractual agreements with companies that have registered capital of more than 8.2 billion birr.
Industrial Parks Development Corporation has signed contractual agreements with 10 local companies with a capital of more than 8.2 billion birr.
The agreement was signed by IPDC CEO Aklilu Tadesse and the representatives of the companies.
According to the agreement, ten companies will invest in Bole Lemi, Kilinto, Semera, Adama industrial parks and Dire Dawa Free Trade zone, and will create employment opportunities for more than 7,400 citizens.
It is expected that the companies will take over production sheds and serviced land with complete infrastructure in the mentioned industrial parks and they will move to the production process in a short period of time.