ኮርፖሬሽኑ ለ "ገበታ ለትውልድ" ከ22.7 ሚሊዮን ብር በላይ አስረከበ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለ "ገበታ ለትውልድ" ቃል የገባውን 22 ሚሊዮን 769 ሺ 834 ብር ገቢ አድርጓል።
ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው ከሚገኙ አምራቾች፣ ባለሀብቶችና እና አጋር አካላት በማሰባሰብ ነው ገንዘቡን ገቢ ማድረግ የቻለው።
በዚህም የገበታ ለትውልድን ጥሪ ተቀብሎ ኃላፊነት በመውሰዱ፣ ለመጪው ትውልድ የምትመጥን ኢትዮጵያን ለመገንባት የድርሻውን ስለተወጣ በሚል ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ምስጋናና እውቅና ተችሮታል።
The corporation handed over 22.7 million birr to the "Dine for Generation"
Industrial Parks Development Corporation has raised 22 million 769 thousand 834 Birr which it promised to "Dine for Generation".
The corporation was able to raise the money from manufacturers, investors and partners who are engaged in investment in industrial parks.
IPDC received the praise and recognition from the Prime Minister's Office for accepting the call of the 'Dine for Generation' and taking responsibility for doing its part to build prosperous Ethiopia for the next generation.