• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 11 months, 1 week ago
  • 236 Views

የኮርፖሬሽኑ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም

በጅማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኮርፖሬሽኑ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ላለፉት ሁለት ቀናት በጅማ ከተማ ሲያከናውነው የቆየው የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል።

በማጠቃለያውም የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት በከፍተኛ ትኩረት መከናወን ባለባቸው ስትራቴጂክ የእቅድ ስራዎች ፤ የተጀመሩ የአገልግሎት አሰጣጥና የአሰራር ሪፎርሞችን በማጠናከር ፤ ተቋማዊ አሰራርን እና የኮርፖሬት የስራ ባህልን በማሳደግ ፤ በጥብቅ የስራ ዲሲፕሊን እና በበሰለ አመራር ሰጪነት ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠርና ተቋሙ የተቋቋመለትን አላማና ግብ ለማሳካት በሚቻልባቸው አካሄዶች ላይ የስራ መመሪያና አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

ከማጠቃለያ ፕሮግራሙ ባሻገር በዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ መሪነት ሁሉም የመድረኩ ተሳታፊ ከፍተኛ አመራሮችና የስራ ኃላፊዎች የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው የተመለከቱ ሲሆን ዋና ስራ አስፈፃሚው በፓርኩ ከሚገኙ አምራች ኩባንያዎች ጋር ፍሪያማ ውይይት አድርገዋል።

ከጉብኝቱ በተጨማሪ በፓርኩ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተከናውኗል።

The evaluation of IPDC's 9-month performance, which has been taking place in Jimma city, has been completed.

The evaluation of the performance of the 2015 fiscal year 9-month plan, which IPDC has been conducting in Jimma City for the past two days, has been completed.

In conclusion, the CEO of the corporation, Aklilu Tadesse, has laid down work instructions and direction on strategic planning works, operational reforms, strict work discipline and ways to create a comfortable work environment with genuine leadership.

Apart from the closing program, all the senior leaders and officials of IPDC with the CEO took a tour of the current activities of the Jimma Industrial Park and the CEO had a lively discussion with the manufacturing companies in the park.

In addition to the tour, a green legacy program was held in the park.