የሩሲያ የመኪና አምራች ኩባንያዎች በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ
ከሩሲያ የላዳ እና ጋዝ ግሩፕ መኪና አምራች ኩባንያዎች የመጡ ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ለተወካዮቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ፣ ስለዘርፉ ማበረታቻዎች እንዲሁም በአፍሪካ ግንባር ቀደም ስለሆነው የድሬዳዋ የነጻ ንግድ ቀጠና አጠቃላይ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ኃላፊዎቹ የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
ኩባንያዎቹ በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ ገበያዎች ለጤና ተቋማት፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለግልና ለህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ የሚውሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ ታዋቂ መሆናቸው ይታወቃል። ተወካዮቹ በተለይም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት በማድረግ የተለያዩ ምዴል ምርቶችን በኢትዮጵያ ገበያ የማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
Russian car manufacturing companies expressed their desire to invest in Dire Dawa Free Trade Zone
Representatives from Russia's Lada and Gaz Group car manufacturing companies discussed with Mr. Shiferaw Solomon, Deputy CEO of IPDC.
The representatives were briefed on the favorable investment situation in the industrial parks, the incentives for the sector and the Dire Dawa Free Trade Zone.
The officials toured Bole Lemi and Kilinto Industrial Parks and observed the activities and production process.
The companies are famous in Europe, South America and Africa markets for providing different models of vehicles for health facilities, security agencies, cargo services and private and public transport sectors.
The representatives stated that they are interested in offering various model products in the Ethiopian market by investing in Dire Dawa Free Trade Zone.