• Striving for eco industrial park
logo

የታንዛኒያ ልዑካን ቡድን አባላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ልምድ ለመቅስም ጉብኝት አካሄዱ

የታንዛኒያ ልዑካን ቡድን አባላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ልምድ ለመቅስም ጉብኝት አካሄዱ

የታንዛኒያ የማህበራዊ ዋስትና ፈንድ ልዑካን ቡድን አባላት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፉት አስር ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትና አስተዳደር ያካበተውን ልምድ በአካል ተገኝተው መመልከታቸው ጠቃሚ መሆኑን ገለጹ።

ለልዑካን ቡድኑ አባላት ስለ ኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ፣ ስለ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች አስተዳደር፣ ስለ ኢንቨስትመንት ፍሰት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ እንዲሁም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ስላላቸው አስተዋጽኦ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ገለጻውን የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በለጠ እና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ደንበኞች አገልግሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ታደሰ አቅርበዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ተቋማቸው ከማህበራዊ ዋስትና የሰበሰበውን ሀብት በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ዘርፍ ለማዋል ከመወሰኑ በፊት ልምድ ለመቅሰም ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን ገልጸዋል።

በኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ከተደረገላቸው ገለጻ በተጨማሪ፣ በቂሊንጦና ቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች በመገኘት ያደረጉት የመስክ ምልከታ ብዙ ተግባራዊ ልምዶችን እንዲገነዘቡ እንዳገዛቸው አመላክተዋል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ፣ የታንዛኒያ ልዑካን ቡድን በሀገራቸው እየተከናወነ ያለውን የኢንዱስትሪ ልማት በፓርኮች ልማት ኢንቨስትመንት ለማጠናከር የሚያግዝ ልምድ ከኢትዮጵያ ለመቅሰም መሆኑ ተገልጿል።