የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የአመታት የኦዲት ባክ ሎግ መፍታት መቻሉ ስኬታማ ስራ ነው - የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ልማት ኮርፖሬሽን የአመታት የኦዲት ባክ ሎግ መፍታት መቻሉ ከሌሎች የመንግስት ልማት ድርጅቶች አንጻር ሲታይ ስኬታማ ስራ ነው አሉ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መለስ መና፡፡
ዋና ሰብሳቢው ይህን ያሉት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በአዳማ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የመስክ ምልከታ አድርገው የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ ስራ በተመለከተ በተካሄደ ውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ መለስ መና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገቢን ከማሳደግ፣ ባለሀብት ከመሳብ ፣ ከውጪ ምንዛሬ ግኝት እና የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ ያስመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኮሚቴው ዋና ሰብሳቢው ባለሀብት የመሳብ ጉዳይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አበክረው የገለጹ ሲሆን የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ኮሬ ኮርፖሬሽኑ ለዜጎች ስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ፣ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በራስ አቅም ለመስራት መሞከሩ፣ የኦዲት ባክ ሎግ መፍታት፣ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት መስኮችን ማስፋት መቻሉ በጥንካሬ የሚነሳ መሆኑን አውስተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኮርፖሬሽኑ እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የአምስት አመት እስትራቴጂክ እቅድ ቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አብራርተው ይህም ኮርፖሬሸኑን ወደ ቀጣይ የእድገት ምራፍ ያሻግራል ብለዋል፡፡
እቅዱ ተቋሙ እንደ መንግስት የልማት ድርጅት እና እንደ አንድ የፖሊሲ ተቋም ለዜጎች ምቹ የስራ እድል ለመፍጠር ፣ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት፣ የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ፣ ለሀገር ውስጥ አምራቾች የገበያ ትስስር ለመፍጠር እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማረጋገጥ የሚያስችል የዝግጅት ስራ ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#pharmaceuticals
#informationtechnology
#itparks
#africafreetradezone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30