የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ጉብኝት አደረጉ
በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ተገኝተው የዞኑን የስራ እንቅስቃሴ እና የኩባንያዎችን ስራ ጎበኙ፡፡
የምክር ቤት አባላቱን ተቀብለው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ መንግሥት ትኩረት ከሰጠባቸው ዘርፎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማት አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም የምክር ቤት አባላቱ ድጋፍ ክትትልና እገዛ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ ይማም በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንና አጠቃላይ የኮርፖሬሽኑን የስራ እንቅስቃሴና ተግባራት አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ምክር ቤቱ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅን ከማጽደቅ ጨምሮ በቋሚ ኮሚቴው ለሚደረግላቸው የድጋፍና ክትትል ስራዎች በኮርፖሬሽኑ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የምክር ቤት አባላቱ በተጨማሪም በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የሚገኘውን ሽንትስ ጋርመንት ኩባንያ የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም በግንባታ ላይ የሚገኙ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ከ300 በላይ የምክር ቤት አባላት መሳተፋቸው ታውቋል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#KombolchaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30