ዓለም ባንክ ኮርፖሬሽኑ ወደ ቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ባለሀብቶችን ለመሳብ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታወቀ
የዓለም ባንክ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ወደ ቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በመድሀኒት እና ህክምና ቁሳቁስ ምርት ዘርፍ ስመ-ጥር ባለሀብቶችን ለመሳብ የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታወቀ፡፡
የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ማምታ ሙርቲ እና የባንኩ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ም/ፕሬዚዳንት ንዲያሜ ዲዮፕ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አልምቶ የሚያስተዳረው የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የስራ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
የባንኩ አመራሮች ኮርፖሬሽኑ በጤና ዘርፍ ስመጥር የሆኑ ባለሀብቶችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ እንዲገቡ ለማድረግ የሚያደርገውን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚደግፉ ጠቁመው ዘርፉ የሚፈልገውን የሰው ሀብት በመፍጠር ረገድ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡
የባንኩ ከፍተኛ ኃላፊዎች ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ የሚገቡ ባለሀብቶች የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበትን አግባብ ከሀገር ውስጥ ባንኮች ጋር በመሆን ሊያመቻቹ የሚችሉበትን እድልም እንደሚያዩ አመላክተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ምክትል ሚኒስትር ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመሰረተ ልማት ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ ጸጋዬ ዘካሪያስ፣ የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪያጅ አቶ ቶሎሳ በዳዳን ጨምሮ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሀብቶች ተገኝተዋል፡፡
ቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በአፍሪካ ብቸኛው ጤና ላይ ትኩረቱን ያደረገ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ሲሆን ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር መልማቱ ይታወቃል፡፡
World Bank pledges to support the Corporation’s efforts to attract anchor investors into KSEZ
Senior leadership of the World Bank has pledged to support the Industrial Parks Development Corporation’s efforts to attract anchor investors in the pharmaceutical and medical supplies manufacturing sector into Kilinto Special Economic Zone (KSEZ).
World Bank Vice President Mamta Murthi and the Bank’s Vice President for Eastern and Southern Africa, Ndiame Diop, were briefed about the operatipon of Kilinto SEZ.
Bank officials noted that they support the Corporation’s promotional efforts to bring anchor investors in the health sector to the KSEZ. They also highlighted the importance of focusing on creating the human capital the sector requires.
The Senior World Bank leadership also indicated that they see the potential for facilitating financial support for investors entering the SEZ through cooperation with local banks.
The discussion was attended by Ethiopia’s Minister of Health, Dr. Mekdes Daba; State Minister Frehiwot Abebe; State Minister of Finance Semerita Sewasew; IPDC’s Infrastructure Development Division CEO, Ato Tsegaye Zecharias; Kilinto SEZ Manager, Ato Tolosa Bedada; as well as sector officials and investors.
Kilinto SEZ is the only health-focused special economic zone in Africa and is known for being developed through World Bank financing.
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#KombolchaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#hawasaspecialeconomiczone
#GIZ
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30