በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በቅንጅት መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ
በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የአምራች ኢንዱስትሪ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ እና የብሄራዊ አምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ ገለጹ፡፡
አምባሳደሩ ይህን የገለፁት የብሄራዊ አምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል አባላት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ስር የሚተዳደሩትን የቦሌ ለሚ እና ቂልንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሥራ እንቅስቃሴን በጎበኙበት ወቅት ነው ፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ካውንስሉ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ ከኃይል አቅርቦት፣ በመሠረተ ልማት እንዲሁም ከወስን ማስከበር ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶችና የቁልፍ ባለድርሻ አካላት ሚና ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ለካውንስል አባላቱ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ የስራ እንቅስቃሴና አጠቃላይ ሁኔታ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን በዘርፉ ያለውን ሃገራዊ አስተዋፅኦ ለማሳደግ የቁልፍ ባለድርሻ አካላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
አምባሳደር ግርማ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት መንግስት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ገልፀው ቀጣይነት ያለው ክትትል እና ድጋፍ እንደሚደረግላቸውና ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸው ን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የብሄራዊ አምራች ኢንዱስትሪ ካውንስሉ በቀጣይ በሌሎች ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በመገኘት በዞኖቹ ያለውን የስራ እንቅስቃሴና ያጋጠሙ ማነቆዎች ዙሪያ ምልከታ በማድረግ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica
#mekelespecialeconomiczone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@IPDCETHIOPIA
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30