• Striving for eco industrial park
logo

ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ ነው - ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ

ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ ነው - ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሸን በኩል የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሃብቶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል የመሰረተ ልማት ዝግጁነት ቢኖርም የተለያዩ ዘርፎችን ያማከለ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በቅንጅት መሰጠት ካልተቻለ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳደግ እንደማይቻል የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር ) ገለጹ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ይህን የገለጹት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትናንት በፅህፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት ሲከናውኑ መቆየታቸውን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው አሁንም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ፍላጎት እና አቅሙ ያላቸው ባለሃብቶች ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ገብተው ሀብታቸውን ስራ ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል የቅንጅት ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) በበኩላቸው አቅም ያላቸው ባለሃብቶችን የመለየት፣ የማግባባት ፣በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ላይ ያሉ መሰረተ ልማቶችን የማስተዋወቅ እና በመንግስት በኩል የተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ለባለሃብቶች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች የተጣለባቸውን ሃገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡና ትርፋማ እንዲሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡



#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#EIC
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30