• Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 6 hours, 45 minutes ago
  • 11 Views

ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዓለም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አካባቢን መልሶ ማልማት ስራዎች መካከል ዋናው ነው፡-ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር

#በመትከልማንሰራራት

ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዓለም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አካባቢን መልሶ ማልማት ስራዎች መካከል ዋናው ነው፡-ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት ያካሄደቻቸው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዓለም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አካባቢን መልሶ ማልማት ስራዎች መካከል ዋነኛው መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት የኮርፖሬሽኑን 7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እና የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና ጋር በመሆን በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ባስጀመሩበት ወቅት ነው፡፡

ዶ/ር ፍሰሃ ባለፉት 6 ዓመታት በሃገር ደረጃ በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮችም በራስ አቅም ችግኞችን በማፍላት ከመተከላቸው በተጨማሪ ለተቋማትና ከተማ አስተዳደሮችም ጭምር የማከፋፈል ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

በ7ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በ10ሩ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፣ ሁለቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና በተዘጋጁ የችግኝ ማፍያ ቦታዎች ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በማፍላት ከመትከል በተጨማሪ በየአካባቢያቸው ላሉ ተቋማት በማከፋፈል ላይ መሆናቸውን ዶ/ር ፍሰሃ ገልጸዋል፡፡

ይህ አመታዊ መርሃ ግብር ኮርፖሬሽኑ ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጠውን ትኩረት የበለጠ እንዲያጠናክር ይረዳዋል ሲሉም ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

የዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡

#GreenLegacy
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#SpecialEconomicZones
#madeinethiopia
#madein
#InvestInEthiopia
#InvestEthiopia
#HawassaSEZ
#TextileHub
#PlugAndPlay
#AfricaRising
#manufactureinafrica

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30