የእስራኤል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ገብተው ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ
ከተለያዩ የእስራኤል ኩባንያዎች የተውጣጡ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን አባላት የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን ጎብኝተዋል።
የልዑካን ቡድኑን ያስጎበኙት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ስለሚሰጡ ማበረታቻዎች፤በመንግስት የተደረጉ የኢንቨስትመንት ሪፎርሞች፤የልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የስራ እንቅስቃሴና የባለሃብቶች ተሳትፎ እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ትንሳኤ ይማም በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ስላለው የባለሀብቶች እንቅስቃሴና የባለሀብቶች ተሳትፎ፤በስራ እድል ፈጠራ፤በእውቀትና ክህሎት ሽግግር እንዲሁም የመሰረተ ልማት አቅርቦትና ማበረታቻዎች ዙሪያ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
የልዑካን ቡድኑ በበኩላቸው በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ያለው የመሰረተ ልማት አቅርቦትና የባለሀብቶች የስራ እንቅስቃሴ ጥሩ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ገብተው ለመስራት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
Israeli Business Delegation Visits the Bole Lemi Special Economic Zone
Israeli Business Delegation paid a working visit to Industrial Parks Development Corporation’s Bole Lemi Special Economic Zone.
Mr. Zemen Junedi, Chief Investment Promotion and Marketing Officer of IPDC, briefed the delegation on incentives offered in special economic zones, government investment reforms, investor activities and participation, and investment options.
Mr. Tinsae Yimam, General Manager of the Bole Lemi Special Economic Zone, provided a briefing on investor activities and participation, job creation, knowledge and skills transfer, infrastructure provision, and incentives within the special economic zone.
The delegation stated that the infrastructure provision and investor activity in the special economic zone were positive and expressed their intent to further expand collaboration.
#IPDC
#KilintoSEZ
#NewBeginnings
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone
#InvestInEthiopia
#SEZ
#BusinessGrowth
#jobcreation
#Israel
#israelbusiness
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30