• Striving for eco industrial park
logo

የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲጫወት ለማስቻል የዘርፉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ይህ የተጠቆመው በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በንግድና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ለመስራት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የውል ስምምነት የተፈራረሙ ኩባንያ ባለቤቶች እና አመራሮች ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በመከሩበት ወቅት ነው፡፡

በውይይት መድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም ከተማ መድረኩ ወደ ነጻ የንግድ ቀጠናው ለመግባት የተፈራረሙ ኩባንያዎችን ስራ ቀልጣፋና ምቹ ለማድረግ መዘጋጀቱን ጠቁመው በየዘርፉ ያላቸውን ጥያቄዎች ለባለድርሻ አካላት እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ነጻ ንግድ ቀጠናውን ተወዳዳሪ ለማድረግ የመንግስት ተቋማት ቅንጅት አስፈላጊ መሆኑን ያወሱት ባለሀብቶች ዓለም አቀፍ ሁኔታውን ያገናዘቡ ወቅታዊ እና ተከታታይነት ያላቸውን ማሻሻያዎች እንዲሚያስፈልጉም አመላክተዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ በንግድና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ያላቸውን ልምድ በማካፈል ነጻ የንግድ ቀጠናው የበለጠ ውጤታማ ሊያደርገው ይችላል ያሉትን ነጥቦች አንስተዋል፡፡

በነጻ የንግድ ቀጠናው ስራዎችን ለማቀላጠፍ የተደረጉ የመንግስት ማበረታቻዎችና ማሻሻያዎች ጥሩ መሆናቸውን የገልጹት ባለሀብቶቹ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ከፍቃድ፣ ከሎጀስቲክ ክፍያ እና ከፋይናንስ ስርዓት ጋር ያሉ ሁኔታዎች ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ጋር እየተገናዘቡ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲሻሻሉ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች ቀጣይነት ባለው መልኩ የነጻ ንግድ ቀጠናውን አሰራር ለማሻሻል እስካሁን የተኬደበትን ርቀት አብራርተው ወደፊትም ሁኔታዎችን እንደ ወቅቱ ሁኔታ ለማሻሻል በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡


#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone
#InvestInEthiopia
#BahirDarSEZ
#BusinessGrowth
#jobcreation
#agroprocessing
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30