አንቴክስ ቴክስታይል በ20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
በአዳማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሚገኘው አንቴክስ ቴክስታይል ኃ.የተ.የግ.ማ በ20 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ኩባንያው ይህን ያስታወቀው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) የኩባንያውን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
ኩባንያው በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ የጀመራቸው የማስፋፊያ ስራዎች በአጭር ጊዜ አጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡
አንቴክስ ቴክስታይል ምቹ የስራ ከባቢ ለሰራተኞቹ ለመፍጠር በማሰብ ለሰራተኞች መኖሪያ እየገነባ ሲሆን የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ስራውን ለማስፋት የሚያስችሉ ተጨማሪ የግንባታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ኩባንያው ምቹ የስራ ከባቢ ለሰራተኞቹ ለመፍጠር 3 ብሎኮችን የያዘ 6000 ሰራተኞችን ማስተናገድ የሚችል የመኖሪያ ህንጻን እየገነባ ነው፡፡
አንቴክስ ቴክስታይል በአዳማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከ4500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድልን የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ አምስት ዓመታት የሰራተኞቹን ቁጥር ወደ 20ሺ ለማሳደግ ተግባራዊ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
Antex Textile Conducting 20 million USD Expansion Work
Antex Textile Ethiopia Private Limited Company has announced a major expansion project, with an estimated cost of 20 million USD.
The announcement was made during a visit by Dr. Feseha Yitagesu, the CEO of the Industrial Parks Development Corporation.
Dr. Feseha assured the company that his office would provide full support to ensure the timely completion of the expansion.
The project includes the construction of factory sheds and residential quarters for staff, which will significantly boost the company’s export potential.
Currently, a three-block residential building is being built to accommodate more than 6,000 employees. At present, Antex Textile has created over 4,500 job opportunities, and once the expansion is completed, this number will rise to 20,000.
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone
#InvestInEthiopia
#BahirDarSEZ
#BusinessGrowth
#jobcreation
#adamaspecialeconomiczone
#Zeroliquiddischarge
#antexttextile
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30