በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በ500 ሚሊዮን ብር ስራ የጀመረው ፓሮን ትሬዲንግ የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ
በባህር ዳር ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ500 ሚሊዮን ብር ካፒታል ከበቆሎ ምርት ስታርች ለማምረት ስራ የጀመረው ሃገር በቀል ኩባንያ የማሽን ተከላ ስራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡
የባህር ዳር ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ጥሩየ ቁሜ እንደገለጹት ኩባንያው 2 ሄክታር መሬት ተረክቦ የግንባታ እና የማሽን ተከላ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው ኩባንያው ከ4000 በላይ ከሚሆኑ አርሶ አደሮች ጋር ዘላቂ የሆነ ምርት አቅርቦት እንዲኖረው የሚያስችል የገበያ ትስስር ፈጥሯል ብለዋል፡፡
ኩባንያው ምርቱን ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ለኮርፖሬሽኑ ባስገባው ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ገልጿል፡፡
ፓሮን ትሬዲንግ 592,000 ኩንታል በቆሎን በግብዓትነት የሚጠቀም መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጇ ይህም ለአካባቢው በቆሎ አምራች አርሶ አደሮች ቀጣይነት ያለው ገበያ ትስስር ከመፍጠሩ በተጨማሪ በስራ እድል ፈጠራ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
ኩባንያው አሁን ላይ ለ300 የአካባቢው ወጣቶች ዘላቂ የሆነ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#eco industrial park
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone
#Madeinethiopia
#bahirdarspecialeconomiczone
#africanfarming
#agroprocessing
#parrontrading
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30