የጃፓን ባለሀብቶች ለቅድመ-ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገለጹ
በቶክዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተካሄደው የ33ኛዉ ኤዢያ፤ አረብ እና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች ለቅድመ-ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገለጹ፡፡
በጃፓን ዋና ከተማ ቶክዮ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ላይ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው ለቅድመ-ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚመጡ ገልጸዋል፡፡
ጃፓናውያኑ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በማምረቻ ፤ በንግድ ፤ ሎጂስቲክ እና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳሳደረባቸው ገልጸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቅድመ-ኢንቨስትመንት ጥናት እና ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ አረጋግጠዋል፡፡
ባለሃብቶቹ በውይይቱ በኢትዮጵያ ስራቸውን ለመስራት የሚያስችል የሰለጠነ ወጣት የሰው ኃይል፤ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ፤ ሰፊ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ገበያ መዳረሻ ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገነቡ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ነጻ ንግድ ቀጠና መኖራቸውን መረዳታቸውን ጠቁመዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኮርፓሬሽኑ የኢንቨስትመንት ሂደቱን ቀልጣፋ በማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ የምትሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን ለባለሀብቶች አረጋግጠዋል፡፡
ኮርፓሬሽኑ ባለፉት ጥቂት አመታት በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ድሬ ዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና የጃፓን ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ከ450 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ያስመዘገቡ 22 በጃፓናውያን እና በኢትዮጵያውያን ሽርክና ተቋቁመው ስራ የጀመሩ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ በቦሌ ለሚ የልዩ ኢኮኖሚ ዞን የሚስጥራዊ ህትመት ለማከናወን ከመንግስት ተቋማት ጋር በሽርክና እየሰራ ያለው ቶፓን ግራቪቲ እና በሐዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሶላር ፓኔል ለማምረት የሙከራ የምርት ሂደት የሚገኙው ቶዮ ሶላር በአብነት ይጠቀሳሉ፡፡
Japanese Investors to Visit Ethiopia for Pre-Investment Assessment
Japanese investors who participated in the 33rd Asia, Arab, and Africa Investment Forum, hosted by the Ethiopian Embassy in Japan, have decided to visit Ethiopia for a pre-investment assessment.
The investors are interested in sectors including manufacturing, trade and logistics, agricultural drone production, pharmaceuticals and cosmetics, robotics technology, and chemical manufacturing.
According to the investors who attended the forum in Tokyo, the event provided valuable insights into Ethiopia’s labor market, natural resource potential, regional market, and infrastructure capabilities.
Feseha Yitagesu, PhD, CEO of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC), reassured the investors that the corporation will assist them at every step to facilitate their pre-investment assessment visit.
IPDC has been actively promoting investment opportunities in Ethiopia’s Special Economic Zones (SEZs) to potential investors in Japan. Notable success stories include Japanese security printing giant Toppan Gravity and solar cell leader Toyo Solar.
Currently, more than 22 companies owned by Japanese firms or joint ventures operate in Ethiopia. These companies have invested over 450 million USD and created more than 3,000 jobs, playing a significant role in the growth of Ethiopia’s economy.
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzone
#japaninvestment
#specialeconomiczone
#japan
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30