• Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 2 months ago
  • 143 Views

ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችንና ነጻ ንግድ ቀጠናን ለቻይናውያን ያስተዋወቀ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተካሄደ

ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችንና ነጻ ንግድ ቀጠናን ለቻይናውያን ያስተዋወቀ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተካሄደ 

ከ 200 በላይ ከቻይና  ጃንግዙ ግዛት  የመጡ የቢዝነስና የንግድ  ልዑካን ቡድን እና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ጃንግዙ የኢኮኖሚና የንግድ  ኮንፈረንስ የካቲት 18/2017 በአዲስ አበባ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ 

በኮንፈረሱ የተሳተፉት የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲን ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለኢንቨስትመንት ያዘጋጀቻቸውን ምቹ ሁኔታዎች ፤ መንግስት በተለይም ለቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት በሰጠው ትኩረት ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር ለመፍጠር የተደረጉ የሪፎርም ማሻሻያዎችና ማበረታቻዎች ላይ ገለፃ አድርገዋል። እንዲሁም ኮርፓሬሽኑ አልምቶ በሚያስተዳራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ባሉ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችና አማራጮች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለተሳታፊዎች ሰጥተዋል፡፡

በመድረኩ የቻይናውያን ባለሀብቶች ተሳትፎ በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቻችን የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል ያሉት አቶ ዘመን ይህንን ተሳትፎ የበለጠ ለማሳደግ ኮርፓሬሽኑ ከምንግዜውም  በላይ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም ከግዛቲቱ የመጡ የንግድና የቢዝነስ ልዑካን ቡድን አባላት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቻችንና በ ድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኮርፓሬሽኑ ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የቻይና ባለሀብቶች በተለያየ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና እና በሐዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በቴክስታይል እና አልባሳት ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘው wuxi No 1 cotton Ethiopia textile plc  ከቻይናዋ ጃንግዙ ግዛት ኢንቨስት ካደረጉ ኩባንያዎች መካከል ለአብነት የሚጠቀስ ነው ፡፡


Ethio-China Jiangsu Economic and Trade Conference Highlights Investment Opportunities in SEZs in Addis Ababa

The Ethio-China-Jiangsu Economic and Trade Conference, which attracted over 200 business and trade delegates from Jiangsu Province, China, as well as senior government officials, was held at the Adwa Victory Memorial Museum Hall on February 25, 2025.

Mr. Zemen Junedin, Chief Investment Promotion and Marketing Officer of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC), emphasized Ethiopia’s commitment to creating a favorable investment climate for foreign investors. He outlined the government’s reforms and incentive packages designed to encourage foreign direct investment, particularly in the country’s Special Economic Zones (SEZs).

Mr. Zemen provided detailed insights into the opportunities available within Ethiopia's SEZs and the Free Trade Zone in Dire Dawa, all of which are managed by IPDC. He underscored the significant role Chinese investors are expected to play in the development of these zones and urged the Jiangsu business and trade delegation to consider investing in the SEZs operated by IPDC.

Several Chinese investors are already engaged in various sectors within the SEZs managed by the corporation. A prime example of this growing collaboration is Wuxi No. 1 Cotton Ethiopia Textile PLC, a company operating within both the Dire Dawa Free Trade Zone and the Hawassa Special Economic Zone, focused on the textile and clothing sector. This partnership exemplifies the deepening ties between Ethiopia and Jiangsu Province of China.

#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia 
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark 
#Investment 
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone 
#madeinethiopia
#EthiopiaRising 
#AfricaTheFuture 
#InvestmentHub 
#innovations  
#EconomicGrowth 
#ddftz
#freetradezone
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/ 
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial 
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc 
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial 
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial 
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et 
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622 
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia 
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30