• Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 month ago
  • 143 Views

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በ60 ሚሊዮን ዶላር ስራ የጀመረው ቶዮ ሶላር የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ በ60 ሚሊዮን ዶላር ስራ የጀመረው ቶዮ ሶላር የሙከራ ምርት ማምረት ጀመረ

በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተለያዩ ሶላር ፓኔሎችን ለማምረት የገባው የጃፓኑ ቶዮ ሶላር ኩባንያ የማሽን ተከላ ስራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ የሙከራ ምርት በማምረት ላይ የሚገኘውን የቶዮ ሶላር ኩባንያን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባ ኮርፖሬሸኑ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በወቅቱ የኩባኒያው የስራ ኃላፊዎች ኩባንያው የግንባታ ስራውን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ መጋቢት አጋማሽ ላይ በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንደሚገባ የኩባንያው አመራሮች ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው በተያዘው በጀት ዓመት በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ለመጀመር ከኮርፖሬሽኑ ጋር ተፈራርሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን ምርቶቹንም ወደ መካከለኛው ምስራቅ ፤ ህንድ እና አሜሪካ እንደሚልክ አስታውቋል፡፡

ቶዮ ሶላር ኩባንያ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ሶስት ሄክታር የለማ መሬት እና የማምረቻ ሼድ ተረክቦ ስራ የጀመረ ሲሆን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ቬትናም ውስጥ የሶላር ፓናል ማምረቻ ፋብሪካ እንዳለው ይታወቃል፡፡

ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት ሲገባ ከ1000 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ቋሚ የስራ እድልን ይፈጥራል፡፡

Toyo Solar Commissions Trial Solar Panel Production at Hawassa Special Economic Zone

Japanese solar giant, Toyo Solar, has commenced trial production of solar panels at the Hawassa Special Economic Zone (HSEZ).

The company, which has invested over 60 million US dollars in the zone, has successfully completed the installation of its machinery and launched test production.

Toyo Solar signed a contract with the Industrial Parks Development Corporation to initiate solar panel production in HSEZ at the beginning of this budget year. Upon full operational capacity, the company plans to export its products to markets in the Middle East, India, and the United States.

Dr. Fiseha Yitagesu, CEO of the Industrial Parks Development Corporation, recently visited the site to assess the company’s progress. He expressed his commitment to continue supporting Toyo Solar in all aspects of its operations.

The company has leased developed land and factory sheds covering more than three hectares within the HSEZ premises. Once fully operational, Toyo Solar is expected to provide permanent employment opportunities for over 1,000 citizens.

#IPDC10thAnniversary

#anniversary

#IPDC

#PMOEthiopia

#striving_for_eco_industrial_park

#industrialpark

#ecoindustrialpark

#Investment

#ForeignDirectInvestment

#Importsubstitution

#exportprocessingzo

#specialeconomiczone

#madeinethiopia

#EthiopiaRising

#AfricaTheFuture

#InvestmentHub

#innovations

#EconomicGrowth

#toyoSolar

#japan

#japaninvestment

በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/

በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial

በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc

በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial

በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial

በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et

በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622

በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia

በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot

በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30