የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮርፖሬሽኑን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገመገመ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር ወደ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ መዛወሩን ተከትሎ የኮርፖሬሽኑን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸምን ለመጀመሪያ ጊዜ ገምግሟል፡፡
ኮርፖሬሸኑ ባለፉት 6 ወራት በ10 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች፤በ2 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና በውጭ ምንዛሬ ግኝት፤ በተኪ ምርት፤ በስራ እድል ፈጠራ፤በገበያ ትስስር ላይ ያከናወናቸውን ተግባራት በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ ኮርፖሬሽኑ በመጀመሪያ 6 ወራት ያስመዘገበው ገቢ የእቅዱን 133 ፕርሰንት መሆኑን ጠቁመው ለዚህም ሀገሪቱ የተገበረችው የውጪ ምንዛሬ አስተዳደር ለውጥ አስዋጽኦ ማበርከቱን አብራርተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከኢንዱስትሪ ፓርክ አልሚ እና አስተዳዳሪነት ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች አልሚ እና አስተዳደሪ የተሸጋገረ መሆኑን ያወሱት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተቋሙ እንደ አዲስ እራሱን ማስተዋወቅ እንዳለበት ጠቁመው ኮርፐሬሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት ያስመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ዶ/ር ብሩክ በተጨማሪም ተቋሙ የሚመዘንበት አመላካች መለኪያዎች እንደ ቢዝነስ ተቋም ሊሻሻል እንደሚገባ እና ኮርፖሬሽኑ አሁን ካስመዘገበው ውጤት በላይ እንዲያስመዘግብ ተገቢው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሃ ይታገሱ ኮርፖሬሽኑ እየተጠቀመባቸው ያሉ የስራ አፈጻጸም መለኪያዎች የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ በሚመጥን መልኩ ለማስተካከል ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ገልጸው ለዚህም ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ መሆኑን ገልጸውላቸዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራር አባላት ከግምገማው በተጨማሪ የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠናን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
EIH Reviews IPDC’s First Half Performance for the Budget Year
Ethiopian Investment Holdings (EIH) has reviewed the first half performance of the Industrial Parks Development Corporation (IPDC) for the first time.
The corporation presented its six-month performance report, highlighting key areas such as foreign revenue generation, import substitutions, market linkages, and revenue generation.
According to Feseha Yitagesu (PhD), CEO of IPDC, the corporation has achieved 133% of its planned revenue target in the past six months of the budget year.
“The surge in revenue is partly attributed to changes in the forex regime change, “he said.
Brook Taye (PhD), CEO of EIH, expressed optimism about the corporation's performance, calling it encouraging. He emphasized the importance of rebranding IPDC as it transitions from developing and managing industrial parks to also overseeing Special Economic Zones (SEZs).
Dr. Brook highlighted the need to adjust the corporation's key performance indicators (KPIs) to focus more on financial ratios. He expressed hope that the corporation will become even more profitable in the months ahead, and reiterated EIH's continued support in achieving these goals.
In response, Dr. Feseha said that efforts are underway to enhance the corporation's KPIs.
In addition to the performance review session, the management of both IPDC and EIH visited the Dire Dawa Free Trade Area, Ethiopia's first free trade zone.
#IPDC10thAnniversary
#anniversary
#IPDC
#PMOEthiopia
#striving_for_eco_industrial_park
#industrialpark
#ecoindustrialpark
#Investment
#ForeignDirectInvestment
#Importsubstitution
#exportprocessingzo
#specialeconomiczone
#madeinethiopia
#EthiopiaRising
#AfricaTheFuture
#InvestmentHub
#innovations
#EconomicGrowth
#EIH
#ddftz
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/@industrialparksdevelopment622
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@ipdc_ethiopia
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30