"ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት የሚመጥን የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር በትኩረት ይሰራል" - ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)
በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ለዘመናት የቆየውን ታሪካዊ ግንኙነት የሚመጥን የሩሲያ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ተሳትፎ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና እንዲኖር በትኩረት እንደሚሰራ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር ) ገለጹ፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት በሩሲያ ሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሮዛ የሩቅነህ ጋር በበይነ መረብ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
ዶ/ር ፍስሃ በበይነ መረብ ውይይቱ የሩሲያ ባለሃብቶች በአግሮፕሮሰሲንግ ፤ በማኑፋክቸሪግ ፤ በፋርማሲዩቲካል ፤ በአዉቶሞቢል እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸው ለዚህም ሩሲያ ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም ከኤምባሲው ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል፡፡
በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሮዛ የሩቅነህ በበኩላቸው ሁለቱ ሃገራት በፖለቲካና በኢኮኖሚ ያላቸው ትብብር ታሪካዊ ከመሆኑ ባሻገር አሁን ላይ ሩሲያውያን ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ለፍላጎቱ ተግባራዊነት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ በቀጣይ በሩሲያ በሚካሄዱ አለምአቀፍ የቢዝነስና የኢንቨስትምንት ፎረሞች በመሳተፍ ፍላጎት ካሳዩ ኢንቨስተሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን በማካሄድ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ የሩሲያ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚሰራ ተመላክቷል።
'We will work diligently to ensure that there is an investment flow that matches the historical relationship between Russia and Ethiopia' - Fisseha Yitagesu (Dr.)
Industrial Parks Development Corporation CEO, Fisseha Yitagesu (Dr.), stated that efforts will be to make the participation of Russian investors in industrial parks and free trade zone in Dredawa suits the historical relationship between Ethiopia and Russia for centuries.
The CEO stated this during an online discussion with the Deputy Ambassador of the Ethiopian Embassy in Moscow, Rosa Yeruqneh.
Dr. Fisseha additionally mentioned that works are being done for Russian investors to invest in agroprocessing, manufacturing , pharmaceutical, automobile and technology sectors, and for this IPDC will work with the embassy to use the potential of Russia.
The Deputy Ambassador of the Ethiopian Embassy in Moscow, Rosa Yeruqneh, said that the political and economic cooperation between the two countries is historic, and that Russian investors are currently interested in investing in industrial parks.
In the discussion, it was pointed out that by participating in the international business and investment forums held in Russia, bilateral discussions will be held with investors who have shown interest, and by introducing investment options in industrial parks and the Free Trade Zone of Dredawa, efforts will be made to increase the participation of Russian investors.