• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 3 weeks, 6 days ago
  • 115 Views

ዲያስፖራውን በኢንቨስትመንት ተሳታፊ ማድረግ

ዲያስፖራውን በኢንዱስትሪ ፓርኮች  ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችሉ የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ተዘጋጅተዋል:-አቶ ዘመን ጁነዲን 

 በመላ ሀገሪቱ በተገነቡት ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና   ዲያስፖራውን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መዘጋጀታቸውን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል  ስራ አስፈጻሚ ዘመን ጁነዲ ገለፁ።

 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዳያስፖራውን በኢንዱስትሪ ፓርኮርች ውስጥ በስፋት ማሳተፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ዘመን ጁነዲን ኮርፖሬሽኑ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ  13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና አስፈላጊውን መሰረተ ልማት እና የኢንቨስትመንት አማራጮች ማዘጋጀቱንና ዲያስፖራው በተለያዩ መንገዶች ያካበተውን አቅምና በዘርፉ ያለውን ዕድል ይበልጥ ለመጠቀም ሁለቱ ተቋማት ተቀራርበው መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

አቶ ዘመን በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኮች  የአገር ውስጥ ባለሀብቶች  ያላቸው ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን አንስተዉ በዚህም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ፤ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን በማረጋገጥ ላይ  ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር  በላይነህ አቅናውም በበኩላቸው  አገልግሎቱ የዳያስፖራውን ተሳትፎ በማሳደግ ለሀገራዊ ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ማጎልበት እንዲቻል ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።

በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከአገልግሎቱ ጋር በትብብር መስራቱ  በኢንዱስትሪ ልማትና በማኑፋክቸሪግ ዘርፍ ዳያስፖራው ያለውን ተሳትፎ ከማሳደግ በተጨማሪ የሀገር ልማትን በሀገር ልጆች የማሳካት ዕድልን እንደሚያሰፋ አቶ በላይነህ ጨምረው ገልፀዋል።

የሁለቱ ተቋማት ትብብር በኢንዱስትሪ ዘርፍ ዳያስፖራው ያለውን ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ ኢትዮጵያ መር የሆኑ ውጤታማ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር  በጋራ እንደሚሰሩ በውይይቱ  ተገልጿል።