• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months, 2 weeks ago
  • 414 Views

ኑ አብረን እንስራ

“ኑ አብረን እንስራ”
የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዘመናዊ  ክሊኒክ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ  ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የንግድ ቀጠና ለኢንቨስተሮች እንዲሁም ለሰራተኞች የሚሆኑ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችንና የተለያዩ አገልግሎቶችን በኢንቨስትመንት ማዕከሎቹ ያቀርባል። 

ኮርፖሬሽኑ ለኢንቨስተሮቹ  እና ለፓርኩ ሰራተኞች ከሚያቀርባቸው አገልግሎቶች መካከል የተሟላ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አንዱ ሲሆን ይህንንም አገልግሎት በሁሉም ኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ በተገነቡት የጤና ጣቢያዎች እየሰጠ ይገኛል። 

ለዚህ ጥሩ ማሳያ በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ደረጃውን የጠበቀ  ክሊኒክ አንዱ ሲሆን ክሊኒኩ የትኛውም ቦታ የሚገኝ መካከለኛ ክሊኒክ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዲችል ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።

ክሊኒኩ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ህጋዊ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና እውቅና በመድሀኒት አስተዳደር ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 105/2004 አንቀፅ 16(5) መሰረት ተሰጥቶታል። 

በክሊኒኩ የኢንቨስትመንት ማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ ለህሙማን የሚሆኑ የተለያዩ ለቅድመ ምርመራ የሚረዱ ሳይንሳዊ መለኪያዎች፤ መድሀኒቶች፤ አልጋዎች እንዲሁም መሰል ለመካከለኛ ክሊኒክ የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁሶች በሙሉ ይገኛሉ። 
በዚህ ለኮምቦልቻና አካባቢዋ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ በሆነው የጤናው ዘርፍ አብረን እንስራ እያለ ኮርፖሬሽኑ ይጋብዛል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ 
09-51-41-41-81
09-51-41-41-73