• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months ago
  • 530 Views

የሩሲያ ባለሀብቶች ተሳትፎ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና

"በኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን የኢትዮጵያንና የሩሲያን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚመጥን የሩሲያ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እንፈልጋለን" - ዶ/ር ፍስሃ ይታገሱ

የሩሲያንና የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚመጥን የሩሲያ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲኖር እንፈልጋለን ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሃ ይታገሱ ገለጹ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት የሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር በጽ/ቤት ቤታቸው ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ዶ/ር ፍስሃ ከልዑካን ቡድኑ ጋር በነበራቸው ቆይታ በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ስለሚገኙ ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች ፤ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችና ለኢንቨስተሮች ዝግጁ የተደረጉ መሰረተ ልማቶች ዙሪያ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ከኤምባሲዎች ፤ ከአለም አቀፍ ማህበራትና ልማት ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡

"We want to have Russian investment in our industrial parks that suits the long-term relationship between Ethiopia and Russia" - Dr. Fisseha Yitagesu

We want there to be an investment flow of Russian investors that suits the long-term relationship between Russia and Ethiopia, said Industrial Parks Development Corporation CEO Dr. Fisseha Yitagesu.

The CEO stated this during a meeting with members of the delegation of the Russian-African Economic Cooperation Committee at his office.

During his stay with the delegation, Dr. Fisseha briefed about the favorable investment conditions in the industrial parks under the corporation and the free trade zone of Dire Dawa. He also gave detailed explanation about the investment incentives and infrastructures made available for investors.

Industrial Parks Development Corporation
is working in cooperation with international associations, NGOs and with embassies to increase the flow of investment in industrial parks.