"በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የታየው የሼድ መያዝ ምጣኔ እድገት በሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች መደገም አለበት" - ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ
በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የታየው የሼድ መያዝ ምጣኔ እድገት በሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች በአጭር ግዜ ለመድገም መስራት እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ ገለፁ።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት በዛሬው እለት የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅዊ የስራ እንቅስቃሴ በተመለከቱበት ወቅት ነው።
ዶ/ር ፍሰሀ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነበራቸው ቆይታ በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ ሀገር በቀልና የውጪ ኢንቨስተሮችና ኩባንያዎች ያሉበትን ወቅታዊ የምርት ሂደት ተመልክተዋል። ከምልከታቸውም ባሻገር ከኢንቨስተሮቹ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በእለቱም የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የ11 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በቀጣይ በ100 ቀናት በትኩረት መሰራት የሚገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ120 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ፤ አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ 19 የማምረቻ ሼዶች ያሉት ሲሆን ሁሉም የማምረቻ ሼዶች በሀገር በቀልና በኢንተርናሽናል በባለሀብቶች ተይዘዋል። በፓርኩ በግላቸው የማምረቻ ሼዶችን መገንባት ለሚፈልጉ ኢንቨስተሮች ግን አስፈላጊ የሚባሉ መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ የተሟሉላቸው የለሙ መሬቶች ይገኛሉ።
በዛሬው እለት በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከነበረው መርሀ ግብር ጎን ለጎን በኢንዱስትሪ ፓርኩ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተከናውኗል።
"The increased rate in the shed occupancy seen in Adama Industrial Park should be replicated in other industrial parks" - Dr. Fisseha Yitagesu.
Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu, stated that the increasing shed occupancy rate seen in Adama Industrial Park should be replicated in other industrial parks in a short period of time.
The CEO underlined this while observing the current activities of Adama Industrial Park today.
During his stay at Adama Industrial Park, Dr. Fisseha observed the current production process of local and foreign manufacturing companies in the industrial park. Apart from his observation, he had a discussions with the investors.
In addition, the performance of the 11-month plan of Adama Industrial Park was presented and discussed, and directions were set on the main issues that should be focused on in the next 100 days.
Adama Industrial Park is developed on 120 hectares of land, has 19 production sheds of international standard and all the production sheds are occupied by investors. In the park, fully developed plots are available for investors with necessary infrastructure who want to build their own production sheds.
Today, a green legacy program was held alongside the program at Adama Industrial Park.