• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 3 months, 2 weeks ago
  • 205 Views

በ564 ሚሊዮን ብር በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገነባው ግዙፍ ኩባንያ

በ564 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት አውቶብሶችን የሚገጣጥም ኩባንያ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ 

በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ564 ሚሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ካፒታል የተለያዩ አውቶብሶችን ለመገጣጠም ለሚገነባ ኩባንያ የግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ 

ገሊላ ማኑፋክሪንግ የተባለ ሃገር በቀል ኩባንያ በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ31ሺ ካሬ ሜትር የለማ መሬት ላይ ግንባታውን ለመጀመር የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ማኔጅመንት ፤ በክልሉ ባለስልጣናትና በኩባንያው ባለቤቶች ተቀምጧል፡፡ 

ኩባንያው የግንባታ ምዕራፉን አጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ የተለያዩ አውቶብሶችን በመገጣጠም ለሀገር ውስጥ ገበያና ወደ ውጭ የሚልክ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ስራ ሲጀምርም ለበርካታ የአካባቢው ወጣት ነዋሪዎችና በዘርፉ ለተማሩ ምሁራን የስራ እድልን የሚፈጥር ይሆናል፡፡ 

ገሊላ ማኑፋክቸሪንግ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከቆዳ የሚሰሩ ጫማዎችን ለማምረት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል ተፈራርመው ወደ ስራ ከገቡና በአጭር ጊዜ  ግንባታቸውን እያጠናቀቁ ከሚገኙ ኩባንያዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ሲሆን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክም የገነባው ማምረቻ ስራ ለመጀመር የማሽን ተከላውን አጠናቆ የሙከራ ምርት ለማምረት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ 

Corner stone was laid to build bus assembly company With an investment of 564 million birr, 

Corner stone was laid for the construction of a company that will assemble different types of buses with an investment capital of 564 million birr. 

The corner stone for a local company called Gelila Manufacturing to start construction on 31,000 square meters of service land in Mekele Industrial Park was laid by regional officials, Mekele Industrial park management and the company owners . 

When the company completes the construction and pre operatinal activities  and goes into operation, it will assemble various buses and provides them for local and international market. Additionally it will create job opportunities for many local young citizens and scholars in the field. 

Gelila Manufacturing is one of the leading companies that have signed a contract with the corporation to manufacture leather shoes at Bole Limi Industrial Park and are completing their construction in a short period of time. The company has completed the machine installation and is preparing to produce sample product to start manufacturing in Bole Lemi Industrial Park.